የየካ ክ/ከተማ የወረዳ 12 አስተዳደር ፅ/ቤት በተቋሙ ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት ፅ/ቤቶች የትራንስፓርት አገልግሎት የጭነት፤ የዲኮር ለ 1 አመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
የየካ ክ/ከተማ የወረዳ 12 አስተዳደር ፅ/ቤት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የየካ ክ/ከተማ የወረዳ 12 አስተዳደር ፅ/ቤት በተቋሙ ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት ፅ/ቤቶች የትራንስፓርት አገልግሎት የጭነት፤ የዲኮር ለ 1 አመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በጨረታው ለመሳተፍ የሚገልጉ ተጫራቾች፤
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ፈቃድ፤ የታደሰ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ በድርጅታችሁ ስም ደረሰኝ መቁረጥ የሚችሉ፤ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ እና በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን፤ ጨረታ ለመሳተፍ እንዲችሉ የግብር ግዴታቸውን ስለመወጣታቸው የተሰጠ የምስክር ወረቀት ለተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ) ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት መሆኑን እየገለፅን በ 11ኛው ቀን ከቀኑ በ 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል። ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታ ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በታች በተገለፀው አድራሻ ጨረታው በሚዘጋበት ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ። ዘግይቶ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታውን የማይመለስ የሰነድ መሸጫ 150 ብር (አንድ መቶ ሀምሳ ብር) ብቻ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ብር 2000 (ሁለት ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- አድራሻችን ኮተቤ ገብርኤል መሳለሚያ አካባቢ ወይም ሰንሻይን መንደር ፊት ለፊት ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ግዥ/ዋ/የስራ ሂደት ክፍል ሲሆን
ለተጨማሪ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር፡- 0118931691 በመደወል የሚፈልጉትን መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡- ተቋሙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በየካ ክ/ከተማ የወረዳ 12 አስተዳደር ፋ/ፅ/ቤት
