የደብረ ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ የግል ለግንባታ መስሪያ እና ለፈርኒቸር የሚሆን ጥራት ያለው ፕላይ ውድ ጣውላ አምራች ድርጅት ነው። ስለሆነም ፋብሪካው ለዚህ ምርት ግብዓት የሚሆን 120 ቶን ግሉ ፓቅንድ /Urea formaldehyde powder resing glue/ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የደብረ ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ የግል ለግንባታ መስሪያ እና ለፈርኒቸር የሚሆን ጥራት ያለው ፕላይ ውድ ጣውላ አምራች ድርጅት ነው። ስለሆነም ፋብሪካው ለዚህ ምርት ግብዓት የሚሆን 120 ቶን ግሉ ፓቅንድ /Urea formaldehyde powder resing glue/ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1. በትክክለኛው የስራ መስክ የተሰማራ የንግድ ስራ ፈቃዱን ያሳደሰ።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው።
3. የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1_ 3 የተሰጡትና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸውጋር ማቅረብ አለባቸው።
5. የጨረታታው ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል ።
6.ተጫራቾች ለግሉ ፓውደር ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ 300,000.00 /ሦስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።
7.ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
8. በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ሰርዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
9. ማናኛውም ተጫራች ኦርጅናል የጨረታ ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በካፓኒው የፋውንዴስን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለተከታታይ 16 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ።
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸን በተገኙበት በ16ኛው ቀን/ጨረታው በተዘረጋበት ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፤30 ሰዓይ ላይ በካፓኒው የፋይናስ ቢሮ ወስጥ በይትፋ ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታደግም።
11። የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም በህዝብ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል።
12. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲ.ፒ.ኦ ወይም በሆኔታ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የአሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት።
13. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከካምፓኒው የፋይናስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
14. ከተሰጠው ብዛት ወይም መጠን በታች ቀንሶ መጫረት አይቻልም።
15. አቅራቢው ድርጅት የማስጫኛ እና የማስወረጃ እንዲሁም ሌሎች ወጪውች ሸፍኖ ንብረቱን ለካፓኒው ንብረት ክፍል ያስረክባል።
16. ካምፓኒው አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
