አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተመልካቾችን እያዝናና የሚያስተምር እና ትዉልድ የሚያንጽ አንድ ተከታታይ የቴሌቬዥን ድራማ እና አንድ ተከታታይ የቴሌቬዥን ሲትኮም እና የኢንቴረር ዲዛይን ስራ መግዛት ይፈልጋል
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 17/2015
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
- ሎት 1 ተመልካቾችን እያዝናና የሚያስተምር እና ትዉልድ የሚያንጽ አንድ ተከታታይ የቴሌቬዥን ድራማ እና አንድ ተከታታይ የቴሌቬዥን ሲትኮም
- ሎት 2 የኢንቴረር ዲዛይን ስራ
በድጋሚ የወጣ ጨረታ በኩር ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊዉ ድርጅት መግዛት ይፈልጋል
በመሆኑም ተወዳዳሪዎች ፡_
- የንግድ ወይም ሙያ ፈቃድና የዘመኑ ግብር ከፋይ ሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ ያላቸዉ : ግዥ መጠን 200,000/ሁለት መቶ ሺህ/ ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15/አስራ ምስት ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 104 300 (ሶስት መቶ ብር) ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይቻላል። ሰነዱን በመሙላት የቴክኒክ እና የፋይናስ ሰነዶችን ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶችን በጥንቃቄ በፖስታ ለየብቻ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 ይከፈታል። ነገር ግን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል።
- የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተመሰከረለት ቼክ/ስፒኦ/፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል። ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከፈትበት 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የሚፈለጉት ተከታታይ የቴሌቬዥን ድራማ እና አንድ ተከታታይ የቴሌቬዥን ሲትኮም እና የኢንቴረር ዲዛይን ስራ ብዛትና ስፔስፍኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን።
- የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ በመምጣት መዉሰድ ይቻላል።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 9735 በፋክስ 058 320 7069 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
ባህር ዳር
