በአህስኮድ ምስራቅ አማራ ቅ/ጽ/ቤት የሳኒተሪ እቃዎች አቅርቦትና እንዲሁም የገጠማ ስራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በነጠላ ዋጋ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአህስኮድ ምስራቅ አማራ ቅ/ጽ/ቤት ስር ለሚገኙ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውል ማለትም ለደሴ ዲያግኖስቲክ የኤሌከትሪክ እቃ፣ ለኦሮሞ ዞን አዳራሽ ኤጋ፣ ለአንጎት የአርማታ ብረቶች አቅርቦት እና ለወረባቦ ወረዳ አስ/ቢ/ግ/ ፕ/ጽ/ቤት፤ ለጋዞ ወረዳ አስ ቢሮ ግንባታ፤ ለደሴ ዲያጎንስቲክ ሆስፒታል ፕሮጀክት ለዋድላ ወረዳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ፣ ለኦሮሞ ዞን አዳራሽ፣ ለለጋምቦ ወረዳ አስተዳደር ፕ/ጽ/ቤት የሳኒተሪ እቃዎች አቅርቦትና እንዲሁም የገጠማ ስራዎችን በዋጋ መሙያው ሰነድ ላይ ተለይቶ በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት ህጋዊና ብቃት ካላቸው አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በነጠላ ዋጋ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
ስለዚህ
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት እቃ ዘርፍ ላይ የዘመነ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የማንኛውም የግዥ መጠን ከብር 200,000.00(ሁለት መቶ ሺህ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ) መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ከብር 20 ሺህ በላይ ለሆነ ግዥ የቫት 15% ግማሹን/50%/ እና ከብር 10 ሺህ በላይ ግዥ ሲፈጸም ከተከፋይ ሂሳብ ላይ 2% ዊዘ ሆልዲንግ ታክስ ይቆረጣል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የአገልግሎት ዓይነት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በአህስኮድ የምስራቅ አማራ ቅ/ጽ/ቤት በደሴ ከተማ በአስተዳደርና ፋይናንስ ደጋፊ የሥራ ሃደት ቢሮ ቁጥር 16 እና በአህስኮድ አዲስ አበባ 4ኪሎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ለአንድ የጨረታ ሰነድ በብር 100.00 መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይv ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት አልቆ በ15ኛው ቀን ማግስት በአህስኮድ ምስራቅ አማራ ቅ/ጽ/ቤት/ደሴ ከተማ/ ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4:30 ይከፈታል፤ ተጫራቾች በእለቱ ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል። ያልተገኘ ተጫራችም በጨረታ ሂደቱ ተገዥ ይሆናል፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደሩበትን የእቃ ዓይነት ስፔሲፊኬሽን አይቶ በትክክል ዋጋ በመሙላት የሚጫረቱበትን ዋጋ በአንድ ወይም ወጥ በሆነ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማዘጋጀት በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ ደሴ ከተማ በሚገኘው በአህስኮድ ምስራቅ አማራ ቅ/ጽ/ቤት ግዥ ኦፊሰር ቢሮ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ከማሸጊያው ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራቾች ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት ፐርሰንት) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /cpo/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ቢያንስ ለ3ወር የሚቆይ ማስያዝ አለባቸው።
- አሸናፊው ሲታወቅ ላሸነፈው እቃ የውል ማስከበሪያ 10% በባንከ በተረጋገጠ የhፍያ ትዕዛዝ (በcpo) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ቢያንስ ለ3ወር የሚቆይ በማስያዝ ያሸነፈውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት መጫኛና ማውረጃ እና የቴስት ማሰሪያ ወጭን ጨምሮ ተጫራቹ ችሎ የእቃውን ጥራት በአማካሪ በማረጋገጥ እና ቴስት ለሚያስፈልጋቸው ግብአቶች ቴስት በማሰራት ማለፉ በአማካሪ በማረጋገጥ ያሸነፈውን እቃ ፕሮጀክቶቹ በሚገኙበት መጋዘን ድረስ ገቢ ማድረግ ግዴታ ነው።
- ማንኛውም ተጫራች ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ማቅረብ እንዳለበት ተገንዝቦ ዋጋ መሙላትና መወዳደር ያለበት ሆኖ የሚሞላው የ 1 ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በሚሸጠው ጨረታ ሰነድ ዋጋ መሙያ ፎርም መሰረት ቫትን ያካተተ መሆን ሲገባው በስከርቢቶ ቫት ይጨመርበት ተብሎ ከተጻፈ ተጫራቹ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ እንዳይኖር በጥንቃቄ ይሞላ በአጋጣሚ ስርዝ ድልዝ ከተፈጠረም ፓራፍ ይደረግ ተጫራቾች እኩል ዋጋ በሚያቀርቡበት ጊዜ ኛ ብዛት ላሸነፈው ቅድሚያ ይሰጣል እንደዛም ሆኖ እኩል ከሆነ በእለቱ በተገኙት ተጫራቾች ፊት በአጣ ይለያል፡ ተጫራች ካልተገኘም እጣው በኮሚቴው ይጣላል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ሆኖ ተጫራቹ በዚህ ምክንያት ለሚያወጣው ወጪ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በአል በመገኘት ወይም በስ.ቁ 033 112 4973/033 311 1009 ወይም 011 126 5652 አ/አበባ አህስኮድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ይጠይቁ
- አድራሻ ደሴ ካራ ጉቱ ግብርና ፊትለፊት ከሚገኘው ቢሮ እና አ.አ አራት ኪሎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት
በአህስኮድ ምስራቅ አማራ ቅ/ጽ/ቤት
