በባሌ ዞን የጎባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቋሚ የቢሮ እቃዎች ፣ የጸህፈት መሳሪያዎች ፣ የግንባታ እቃዎች ፣ የጽዳት እቃዎች ፣ የመኪናና የሞተር መለዋወጫ እቃዎች ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ የደንብ ልብሶችና የግብዣ አገልግሎቶችን በግልዕ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር-C-004/6871
በባሌ ዞን የጎባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳዉ ዉስጥ ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚዉል
- ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣
- የጽህፈት መሳሪያዎች፣
- የግንባታ እቃዎች፣
- የጽዳት እቃዎች ፣
- የመኪናና የሞተር መለዋወጫ እቃዎች ፣
- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- የደንብ ልብሶችና
- የግብዣ አገልግሎቶችን በግልዕ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም:- ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ትችላላችሁ።
- ለተጠየቁት የግዢ እቃዎችና አገልግሎቶች ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸዉ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የንግድ ፍቃዳቸዉን ያሳደሱና ዋናዉንና ኮፒዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በፌደራል ወይም በክልል የገንዘብ ጽ/ቤት በአቅራቢነት የተመዘገቡበትንና እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ማንኛውም ተጫራች በጎባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) 10,000 (አስር ሺ) ብር ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይኖርበታል።
- ተጫራቹ የጨረታዉን ሰነድ በአንድ ኮፒ ማዘጋጀትና እንዲሁም የጨረታዉን ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) በኦርጅናል ሰነድ ዉስጥ ማስቀመጥ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ የማይለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በጎባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የባንክ አካዉንት 1000028118175 በማስገባት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ዉስጥ ከጎባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር-5 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ሰአት ድረስ በተዘጋጀዉ የጫረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ በ3:30 ሰአት የጨረታዉ ሳጥን ይታሸግና በዚሁ እለት ከቀኑ በ4:00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በጎባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር ይከፈታል።
- የጨረታዉ የመክፈቻ ቀን በመንግስት የስራ ቀን የማይዉል ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የጨረታዉን ሙሉ ይዘት (ገጽታ) ከጨረታ ሰነድ መረዳት ይችላሉ።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር-0226611238/0913341620
በባሌ ዞን የጎባ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት
