Tender Detail

Tender Details

  • Deadline20 Aug 2022, 10:31 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Event Organizing And Planning

የጉለሌ ክ/ከተማ የወረዳ 02 ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለ2015 በጀት ዓመት የአላቂ የቢሮ ዕቃዎች ፣ የጽዳት ዕቃዎች ፣ የደንብ ልብስ ዕቃዎች የደንብ ልብስ ስፌት ፣ የህትመት ስራ የትራንስፖርት መስተንግዶ እና የኤሌክትሮኒክስ ጥገና እና የአዳራሽ ዲኮር ፣ የመኪና ጎማና ባትሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታቂያ ቁጥር 001/2015

የጉለሌ ከ/ከተማ የወረዳ 02 ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለ2015 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶች ማለትም

  1. ሎት 01 የአላቂ የቢሮ ዕቃዎች
  2. ሎት 02 የጽዳት ዕቃዎች
  3. ሎት 03 የደንብ ልብስ ዕቃዎች የደንብ ልብስ ስፌት
  4. ሎት 04/ የህትመት ስራ የትራንስፖርት መስተንግዶ እና የኤሌክትሮኒክስ ጥገና እና የአዳራሽ ዲኮር
  5. ሎት05/ የመኪና ጎማና ባትሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል በመሆኑም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል
  • ተጫራቾ በተሰማሩበት የስራ መስከ የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
  • ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ የሚወዳደሩት በሚያመረቱት እቃ ወይም ተጨማሪ እሴት ለጨመሩት እቃ ሲሆን ከዚህ ውጪ ለሆኑ እቃዎች የሚወዳደሩት እነደማንኛውም ተጫራች ሰነድ በመግዛት ይሆናል። ተወዳዳሪዎች በሚያመርቱት እቃ ሲወዳደሩ እና ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ወረቀት ሲያመጡ ልዩ ድጋፍ ይደረግላቸዋል።
  • የመንግስት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  • የጨረታ ሰነዱን በጉለሌ ከ/ከተማ ከወረዳ 02 ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 14 በመምጣት ሰነዱን የማይመለስ በብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመግዛት መውሰድ ይኖርባቸዋል
  • የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
  • ጨረታው ጋዜጣ ከወጣበት ቀናት አንስቶ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይቆያል
  • ጨረታው በአስረኛው ቀን 11፡10 ላይ ታሽጎ በአስራ አንደኛው ቀን 3:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉለሌ ከ/ከተማ ወረዳ 02 ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 14 ይከፈታል
  • ተጫራቾች ከጨረታው ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጡት ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  • መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ ብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን ይኸውም
  • ሎት 01/ የአላቂ የቢሮ ዕቃዎች የሚሆን ብር 5000 ብር (አምስት ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል
  • ሎት 02/ የጽዳት ዕቃዎች የሚሆን ብር 6500 ብር (ስድስት ሺህ አምስት መቶ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል
  • ሎት 03/ የደንብ ልብስ ዕቃዎች የደንብ ልብስ ስፌት የሚሆን ብር 3500 ብር (ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል
  • ሎት 04/ የህትመት ስራ የትራንስፖርት መስተንግዶ እና የኤሌክትሮኒከስ ጥገና እና የአዳራሽ ዲኮር የሚሆን ብር 5000 ብር (አምስት ሺህ ብር) እና
  • ሎት 05/የመኪና ጎማ እና ባትሪ የሚሆን ብር 5000 ብር (አምስት ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል እንዲሁም የጨረታ አሸናፊ ከሆኑ በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል
  • ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና የማቅረብ ግደታ ይኖርባቸዋል የሚቀርቡትም ናሙናዎች ተፈትተው የሚታዩ መሆናቸውን ተጫራቾች ማወቅ አለባቸው።
  • ተጫራቾች የአሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • መ/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት የአሸነፉበትን ዋጋ መጠን እና ብዛት 25% ተጨማሪ ትዕዛዝ መጠየቅ የሚችል መሆኑ መታወቅ አለበት።
  • መ/ቤቱ ከውል በፊት እንደአስፈላጊነቱ የእቃውን ብዛት 20% መጨመር ወይም መቀነስ እንደሚችል መታወቅ አለበት

ለተጨማሪ ማብራሪያ

  • አድራሻ፡- ስድስት ኪሎ ከፍ ብሎ ስብሰባ ማዕከል አጠገብ ወደ ሀምሌ 19 መናፈሻ 100 ሜትር ገባ ብሎ
  • ስልከ ቁጥር፡- 011 123 4423 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

የጉለሌ ክ/ከተማ የወረዳ 02 ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

Save Tender