Tender Detail

Tender Details

  • Deadline20 Aug 2022, 9:47 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Event Organizing And Planning

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የገንዳ ቆሻሻ አንሺ መኪና ጥገና ሰርቪስ ፣ የቀላል መኪና ጥገና ሰርቪስ ፣ የታሸገ ውሃ ፣ የሆቴል መስተንግዶ ፣ የደንብ ልብስ ስፌት ፣ የተለያዩ የህትመት ስራዎች ፣ የመኪና ኪራይ ፣ የጀነሬተር እና ሞንታርቦ ኪራይ ፣ የአዳራሽ ዲኮር እና ድንኳን ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2015 ዓ.ም.

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ግዥ አስተዳደር ቡድን የ2015 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን

  1. የገንዳ ቆሻሻ አንሺ መኪና ጥገና ሰርቪስ
  2. የቀላል መኪና ጥገና ሰርቪስ
  3. የታሸገ ውሃ
  4. የሆቴል መስተንግዶ
  5. የደንብ ልብስ ስፌት
  6. የተለያዩ የህትመት ስራዎች
  7. የመኪና ኪራይ
  8. የጀነሬተር እና ሞንታርቦ ኪራይ
  9. የአዳራሽ ዲኮር እና ድንኳን
  10. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና
  11. የቋሚ የቢሮ (ፈርኒቸር) እቃዎች ጥገና
  12. የመኪና እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1.ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣  በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና ጨረታ ላይ ሊያሳትፋቸው የሚያስችሉ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. የግብር ከፋይነት (TIN number) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO

  1. የገንዳ ቆሻሻ አንሺ መኪና ጥገና ሰርቪስ ብር 10,000(አስር ሺህ ብር) ፣
  2. የቀላል መኪና ጥገና ሰርቪስ ብር 7,000(ሰባት ሺህ ብር)፣
  3. የታሸገ ውሃ ብር 2,000(ሁለት ሺህ ብር)፣
  4. የሆቴል መስተንግዶ ብር 2,000(ሁለት ሺህ ብር)፣
  5. የደንብ ልብስ ስፌት ብር 2,000(ሁለት ሺህ ብር)፣
  6. የተለያዩ የህትመት ስራዎች ብር 3,000(ሶስት ሺህ ብር)፣
  7. የመኪና ኪራይ ብር 5,000(አምስት ሺህ ብር)፣
  8. የጀነሬተር እና ሞንታርቦ ኪራይ ብር 1,000(አንድ ሺህ ብር)፣
  9. የአዳራሽ ዲኮር እና ድንኳን ብር 2,000(ሁለት ሺህ ብር)፣
  10. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና ብር 2,000( ሁለት ሺህ ብር)፣
  11. ቋሚ የቢሮ (ፈርኒቸር) እቃዎች ጥገና ብር 2,000(ሁለት ሺህ ብር)፣
  12. የመኪና እቃዎች ብር 10,000(አስር ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ  ከታወቀ ባንክ ለ60 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ  ሆኖ ከጨረታ ሰነዱ ኦርጅናል ቴክኒካል ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት ሲፒኦ በእያንዳንዱ ሎት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ ብር 100.00( አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10(አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ቀን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አዲሱ ገበያ ኖክ ማደያ ጀርባ ያለው የይዞታ አስተዳደር ጽ/ቤት የነበረው ቢሮ ግዥ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ውስጥ በመቅረብ መግዛት ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያው ዋጋ ባዘጋጀነው የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ መሙላት ይኖርባቸዋል። ከላይ የተጠቀሰውን ማስረጃዎች ማለትም ቴክኒካል ኦርጅናል ፣ ቴክኒካል ኮፒ ፣ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ፋይናሻል ኮፒ በተለያየ ፖስታ (4 ፖስታ) በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡45 ሰዓት ታሽጎ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

7. የጨረታው አሸናፊ ለመልካም አፈፃፀም (ለውል ማስከበሪያ) ያቀረቡትን ዋጋ 10% ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

8. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ዝርዝር (specification) መሰረት የሚያቀርቧቸውን ዋጋ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።

9. አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ ከተገለጸበት ከ7 የስራ ቀናት በኋላ በ8ኛ የሥራ ቀን ውል መፈረምና ውል ከፈረመበት ቀን ጀምሮ የአሸነፈባቸውን የአገልግሎት (እቃ ዝርዝር በአሸነፉት መሰረት የተፈለገውን አገልግሎት መስጠት) እቃውን የማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል።

10. ከውል በፊት 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይቻላል።

11. ለመኪና እቃዎች ሳንፕል መቅረብ አለበት።

12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. የሚሞላው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት። ካልተካተተ ግን እንደተካተተ ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን እንገልፃለን።

ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ ስልክ ቁጥር 011 820 9914 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ግዥ አስተዳደር ቡድን

Save Tender