የቅምብቢት ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት በቅምብቢት ወረዳ ስር ላሉ ባለ በጀት መ/ቤቶች የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የቅምብቢት ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት በቅምብቢት ወረዳ ስር ላሉ ባለ በጀት መ/ቤቶች የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ፦
በሥራ ዘርፉ የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ፣ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT 15%) ተመዝጋቢ የሆናችሁ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላችሁ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በቅምብቢት ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ዝርዝር መጠይቆችን የያዘውን ሰነድ በማይመለስ ብር 100 በካሽ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በዝርዝር የተመለከተውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በካሽ ወይም ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ቀን 23/12/2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በዚሁ እለት በቀን 23/12/2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፦
- ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ውሉን ፈጽሞ ዕቃዎችን የማስገባት ግዴታ አለበት።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ (አማራጭ) ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ፡- ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ 78 ኪሎ ሜትር ሸኖ ከተማ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011687 0211/0910 093362 በመደወል ጠይቆ መረዳት ይቻላል።
በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን
የቅምብቢት ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት
