Tender Detail

Tender Details

  • Deadline02 Sep 2022, 9:33 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Event Organizing And Planning

በጉ/ክ/ከ/ፐ/ሰ/የሰው/ሃ/ል/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን የመኪና ጥገና ፣ የድንኳን ኪራይ ፣ የኮምፒዩተር ጥገና ፣ የውሃ ቦቴ ኪራይ ፣ የመኪና ኪራይ ፣ ከሆቴል ውጪ መስተንግዶ ፣ ዲጄና ዲኮር ኪራይ እና የሆቴል መስተንግዶ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

በጉ/ክ/ክ/ፐ/ሰ/የሰው/ሃ/ል/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ለ2015 በጀት ዓመት በፑሉ ስር ለሚገኙ ጽ/ቤቶች የተለያዩ አገልግሎቶችን በአጠቃላይ 8 ሎቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት1. የመኪና ጥገና
  • ሎት2. የድንኳን ኪራይ
  • ሎት3. የኮምፒዩተር ጥገና
  • ሎት4. የውሃ ቦቴ ኪራይ
  • ሎት5. የመኪና ኪራይ
  • ሎት6. ከሆቴል ውጪ መስተንግዶ
  • ሎት7. ዲጄና ዲኮር ኪራይ
  • ሎት8. የሆቴል መስተንግዶ

ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን ፣ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል።

  • ተጫራቾች በሚያቀርቡት ጨረታ ፖስታ ላይ ለየትኛው አገልግሎት እንደሚወዳደሩ በግልጽ ለይተው መጻፍ አለባቸው።
  • ተጫራቾች ድረ-ገፅ (ዌብ ሳይት) ላይ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ እንዳላቸው የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። እንዲሁም አስተዳደሩ ባወጣው ጨረታ ላይ ከውል በፊት 20% መጨመርና መቀነስ ይችላል። ከውል በኋላ ደግሞ 25% መጨመር ይችላል።
  • ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ናሙና ለሚጠይቁ ናሙና ማስገባት አለባቸው።
  • ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው አገልግሎቶች በሙሉ በመስሪያ ቤቱ የቴክኒክ ኮሚቴ ደረጃቸውን የጠበቁ ስለመሆናቸው ይገመገማሉ።
  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫት ያካተተ መሆኑን ወይም ዋጋው ከቫት ውጪ መሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው። ይህ ባይሆን ዋጋው ቫት ያካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
  • ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ
    • ሎት1. 10,000 (አስር ሺህ ብር) ፣
    • ሎት2. 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ፣
    • ሎት3. 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ፣
    • ሎት4. 15,000 ( አስራ አምስት ሺህ ብር) ፣
    • ሎት5. 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) ፣
    • ሎት6. 10,000 (አስር ሺህ ብር) ፣
    • ሎት7. 10,000 (አስር ሺህ ብር) ፣
    • ሎት8. 10,000(አስር ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ በጉ/ክ/ከ/ፐ/ሰ/ሀ/ል/ፅ/ቤት/ፋ/ክ/ሂ/ቡድን ስም በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል። ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 50(ሃምሳ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት ወይም ሰነድ በመክፈል በመንግስት የስራ ሰዓት ጉለሌ ክፍለ ከተማ 6ኛ ፎቅ ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የመንግስት ግዢ አስተዳደር ቡድን ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
  • የጨረታ ሰነዶች በሙሉ በኤንቨሎፕ ታሽገው ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ለየብቻው በማድረግና በማያያዝ ፊርማቸውንና ማህተማቸውን በፖስታዎች ላይ በማኖር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  • የካፒታል መጠናቸው ከብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በላይ የሆኑ ተጫራቾች ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • የጨረታው ጊዜ የሚያበቃው በ10ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት የሚከፈት ይሆናል።
  • ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
  • ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናሉ።
  • ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
  • ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት ጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ይህ ባይሆን ግን ከጨረታ ይሰረዛሉ።
  • ተጫራቾች በንግድ ፈቃዳቸው በስተጀርባ ላይ የተዘረዘሩትን የንግድ ዘርፍ አይነቶች ኮፒ አድርው ማቅረብ አለባቸው። የተጫራቾች ማህተምና የንግድ ፈቃዳቸው እንዲሁም የደረሰኞቻቸው ስያሜ አንድ አይነት መሆን ይኖርበታል።
  • በጨረታ መወዳደሪያ የሚቀርብ ዋጋ ለስድስት ወር ፀንቶ ይቆያል።
  • ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ከመ/ቤታችን ጋር ውል ማስከበሪያ ላሸነፉባቸው ዕቃዎች የጠቅላላ ዋጋውን 10% ሲፒአ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህ ባይሆን ግን በጨረታ ያስያዙት /ሲፒኦ, በቀጥታ ለመንግስት ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛሉ።
  • ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ዘርፍ ዋጋ መሙላት አለባቸው።
  • መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የአገልግሎት ብዛት ቀንሶ ወይም ጨምሮ ከአሸናፊው ድርጅት የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡011 812 5178 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።

በጉ/ክ/ከ/ፐ/ሰ/የሰው/ሃ/ል/ጽ/ቤት

የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን

Save Tender