Tender Detail

Tender Details

  • Deadline20 Jul 2022, 1:43 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Office Machines And Accessories

አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ተሽከርካሪዎችን ፣ ሞባይሎችን ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳት ፣ ለሳሙና ምርት ግብአትነት ብቻ የሚያገለግል ዘይት እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና

የተወረሱ የልዩ ልዩ ዕቃዎችና ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ማስታወቂያ

ቁጥር 01/2015

አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን (ተሽከርካሪዎችን ሞባይሎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳት፣ ለሳሙና ምርት ግብአትነት ብቻ የሚያገለግል ዘይት እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) ባሉበት ሁኔታ በግልፅና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከረቡዕ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑ እንገልጻለን። የደረጃ ምርመራ ያላለፉ የምግብ ዘይቶችን በተመለከተ የሳሙና ማምረቻ ፋብሪካ ያለው፣ ኬሚካል ጨምሮበት ለሳሙና ምርት ግብአትነት ብቻ ለጠቀምና ለሚያርተው የሳሙና አይነት ዘይቱ የምርት ግብአት እንደሚኖን በጽሁፍ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል እና የአወጋገዱን ሂደት በተመለከተ ቅ/ጽ/ቤታችን የሚያስቀምጠውን አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ፍቃደኛ የሆነ ብቻ መጫረት እንዳለበት እናሳስባለን።

በመሆኑም፦

1. በቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን በጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቬሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባትስ የሚኖርበት ሲሆን ለሃራጅ ጨረታ ደግሞ ከጨረታ አንድ ቀን በፊት ይዞ ማስመዝገብ ይኖርበታል።

2. የሚሸጠው ዕቃ ተሽከርካሪ ከሆነ ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ በተ.ቁ 1 የተገለፁ ቅድመ ሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገው የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቬሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል።

3. ተጫራቾች የግልፅ ጨረታውን ሠነድ ዕሮብ ከ4፡00-11፡00 ሰዓት ፣ ሀሙስ እና አርብ ከ2፡00- 11:00 ሰዓት ቅዳሜ ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ሰኞ እና ማክሰኞ ከ2፡00-11፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን የሃራጅ ጨረታውን ደግሞ በተመሳሳይ ቀናትና ሰዓታት በነጻ ማግኘት ይችላሉ።

4. በግልፅ እና በሃራጅ በጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ለተሽከርካሪ ሀራጅ ጨረታ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ቢያንስ ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) ተጫራቹ ማስያዝ አለበት።

5. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።

ተ.ቁ

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

ሀራጅ

እስከ 11/11/2014

ሀምሌ 12/11/2014 4፡00 ሠዓት ጀምሮ ይካሄዳል።

ግልፅ

እስከ 12/11/2014

ሀምሌ 13/11/2014 3:45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4:00 ሠዓት ይከፈታል።

 

6.የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።

7.ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት ከተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል

8.አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል።

9. ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

10. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር:- አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ:- 011-470-8503

ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender