በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ ኮምባይን ዴስክና ጥቁር ሰሌዳ ግዥ ለማከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 10/2014
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ ኮምባይን ዴስክና ጥቁር ሰሌዳ ግዥ ለማከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነ ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት በውድድር መስፈርት መሰረት ለመሣተፍ የሚፈልጉ:
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የግብር የከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን አለባቸው
- ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11:30 ድረስ ከግ/ፋ/ን/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት አለባቸው።
- ጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00–6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ለዚህ አላማ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 9:00 ሰዓት ይከፈታል።ሆኖም 16ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- የጠቅላላ ሽያጭ ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢዎች ብቻ መጫረት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ90 ቀን ጸንቶ የሚቆይ ብር 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ብቻ በሲፒኦ ወይም አንኮንዲሽናል ባንክ ጋራንቲ ብቻ በማቅረብ መወዳደር አለባቸው።
- ጨረታው ለ3ወራት (90 ቀናት) ብቻ ጸንቶ የሚቀይ ይሆናል።
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ማግኘት ይችላል።
- የጨረታ ሰነድ ላይ ከተገለጸው እና በሚዲያ ከታወጀው ጋር ልዩነት በሚፈጠርበት ወቅት በጨረታ ሰነድ ባለው ይስተናገዳል።
- ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሣሰቢያ ፡ ሽያጩ ቫትን ጨምሮ ከብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ከቫት ተመዝጋቢዎች ላይ 50% ቫቱን ቀንሰን የምናስቀር መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 046-221-70-02
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ
ሀዋሳ
