የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት እነ ወ/ሮ ወይንሸት ሽፈራው እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ አሰራት ገ/ማርያም መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/291306፤ 294859 12/2/2013ዓም እና በ5/11/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በልደታ ከ/ከተማ ወረዳ 05 የቤት ቁጥር 428 ካርታ ያለው የግቢው ስፋት 157 ካ/ሜ ቤቱ ያረፈበት 25 ካ/ሜ በፕሮፖርሽን ከግቢው ለቤቱ የሚደርሰው የቦታው ድርሻ ስፋት 10 ካ/ሜ ጠቅላላ በፕሮፖርሽን ለግለሰቡ የሚደርሰው የቦታው ስፋት 35 ካ/ሜ ከጠቅላላው ከግቢውመንግድ የሚነካው 66 ካ/ሜ ከቤት ቁጥር 428 መንገድ የሚነካው 14 ካ/ሜ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 29,980 (ሃያ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ብር) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ለነሐሴ 6 ቀን 2014 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬከቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬት የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶቾ የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት
