የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ ለመኖሪያና ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ የከተማ ቦታዎችን በ26ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ በግልፅ ጨረታ ለማስተላለፍ ያወጣው ማስታወቂያ።
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ
የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
- የጨረታ ዙር............ 26ኛ
- የጨረታው አይነት...... መደበኛ
- የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ ጫጫን ጨምሮ በሁሉም ክ/ከተሞች የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 እና ይህንኑ አዋጅ ለማስፈፀም የአብክመ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ ባወጣው ደንብ ቁጥር 103/2004 በክፍል 3 በአንቀፅ 10 በንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከ"ሀ" እስከ "ሠ" በተዘረዘረው መሰረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ማለትም /ለመኖሪያ ፣ ለንግድ አገልግሎት/ የሚውሉ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል። በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ሰው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000/ አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10 ዘወትር በስራ ሰአት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው መሰረት መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ሁለት የተለያዩ ተመሳሳይ ፖስታዎችን በማዘጋጀት 1ኛ ክፍል ሁለት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን እና ክፍል ሶስት የጨረታ ሀሳብ ማቅረቢያ ሰነዱን 2ኛ ሲፒኦን ሁለቱን ሰነዶች አንዳንድ ኮፒ በማድረግ ኦርጅናሉን ለብቻ ኮፒውን ለብቻ በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግና በፖስታዎቹ ላይ ኦርጅናል ወይም ኮፒ በማለት ለይቶ በመፃፍ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ፖስታውን እስከ 10ኛው(አስረኛው) ቀን 11:00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 7 ኦርጅናሉን ሰነድ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ኮፒውን ሰነድ ደግሞ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው የሚዘጋው ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ 11:00 ሰአት ላይ ይሆናል።
- ቦታውን መጐብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለፀው መርሃ ግብር መሰረት የምናስጐበኝ ይሆናል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው አዳራሽ። ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
- የጨረታ መከፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰአት ላይ ይከፈታል።
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ እና በመምሪያው ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ እንዲሁም በዌብ ሳይት WWW.mudc.Gov.et ማግኘት ይችላሉ።
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ
✨ messages.ai_summary
Debre Berhan City Administration Land Department offers residential and commercial urban plots on lease in all sub-cities, including Chacha, in its 26th round open land-lease tender. Plot details are in the tender document. Open to any interested bidder.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
