የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ በክልሉ በሚገኙ ወረዳዎች የማዕድን ሀብት ጥናት ለማከናወን በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማስጠናት ያወጣው ማስታወቂያ።
የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ በክልሉ በሚገኙ ወረዳዎች የማዕድን ሀብት ጥናት ለማከናወን በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ጥናቱን ማስደረግ ይፈልጋል።
- ተጫራቾች በስራ ዘርፉ የታደሰ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸው፣ የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉና የግብር ግዴታቸውን የተወጡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ሆነው ሁሉንም ሠነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ በማድረግ እና የድርጅታቸውን ማህተም በማሳረፍ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በሰም አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ሠመራ ከተማ ከሚገኘው የአፋር ክልል ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ቁጥር 10 በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርበታል።
- አሸናፊው ድርጅት፤ አሸናፊነቱ ታውቆ ውሉ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ በውሉ መሠረት በየወረዳዎች በመገኘት ጥናቱን ማከናወን ይጠበቅበታል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግልጽ ፖስታ ውስጥ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ሠመራ ከተማ በሚገኘው የአፋር ክልል ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4:00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ቀን በ4:30 ሰዓት ይከፈታል።
- ማሳሰቢያ
* ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ካላንደር የሚዘጋው ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
* ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
* ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0905507228 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ
✨ messages.ai_summary
Afar Regional State Mineral Resources Development Bureau seeks licensed firms to carry out a mineral resource study in woredas across the region, through an open tender. Bidders need a renewed sector licence, TIN, VAT and a tax clearance support letter.
