የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር AAM 03/2019
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር........50,000
- ሎት 2 የፎቶግራፍ መሳሪያዎች ግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር ......50,000
- ሎት 3 የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር ...10,000
- ሎት 4 የጄኔሬተር ግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር .......50,000
- ሎት 5 የደንብ ልብስ ግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር ... 10,000
- ሎት 6 የፅዳት እቃዎች ግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር... 10,000
- ሎት 7 የተሽከርካሪ ጎማዎች ግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር ...10,000
በዚሁ መሠረት ተጫራች ድርጅቶች --
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣ የገቢዎች ታክስ ክሊራንስ እና የቫት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ / በአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000050280873 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት (15) ቀናት የመጫረቻ ሰነዱ ከሰኞ እስከ ሀሙስ እና ቅዳሜን ጨምሮ በምክር ቤቱ የግዥ ንብረት እና ሎጂስቲክስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 105 በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናል እና 1 ኮፒ ፤ የፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጅናል እና 1 ኮፒ በተለያየ ፖስታ ታሽገው ማቅረብ ያለበት ሲሆን፤ አራቱም ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ ታሽገው ከላይ የድርጅቱ ስም፤ የጨረታ መለያ ቁጥር እና ሎት በግልጽ መመልከት አለበት።
- ተጫራቾች የነጠላ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ጦር ሀይሎች፣ የምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 4:30 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ማስገባት አለባቸው። የጨረታው ቴክኒካል ዶክመንት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ምክር ቤቱ በሚያመቻቸው አዳራሽ 5:00 ይከፈታል።
- የጀነሬተር የፎቶግራፍ መሳሪያዎች እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ዝርዝር መግለጫ በፅሁፍ እና በፎቶግራፍ የተደገፈ ካታሎግ ከቴክኒካል ዶክመንት ጋር አብሮ መቅረብ አለበት።
- ለጽህፈት መሳሪያዎች ለደንብ ልብስ እና ለጽዳት እቃዎች ናሙና መቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች በአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ስም በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ወይንም ለ60 ቀን የሚቆይ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው።
- የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ከወለድ ነጻ በሆነ ባንኮች አልያም ከወለድ ነጻ አገልግሎት በሚሰጡ ባንኮች ብቻ የተዘጋጀ መሆን ይጠበቅበታል።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ በእያንዳንዱ ገጽ የድርጅቱ ክብ ማህተምና ፊርማ ማድረግ ፤ እንዲሁም ዋጋ የሚሞላው በም/ቤቱ ዋጋ ማቅረቢያ ብቻ ሆኖ ስርዝ ድልዝ ቢያጋጥም በፊርማ ማረጋገጥ ይኖርበታል።
- 15 ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ(አርብን ጨምሮ ) በቀጣዩ የመንግስት የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት መሰረት ጨረታው ይከፈታል።
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ አምጥቶ የሚያስረክብ መሆን አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች በግዴታ ውስጥ የተካተቱትን ህጎች ማክበር የሚችል መሆን አለበት።
- ጨረታው ለ60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።
- ምክር ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ 09-87-19-99-96 መደወል ይችላሉ።
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት
✨ messages.ai_summary
Addis Ababa Islamic Affairs Supreme Council buys in seven lots by open tender: electronics, photography equipment, stationery, a generator, uniforms, cleaning items and vehicle tyres. Bidders need a renewed licence, TIN, supplier certificate, tax clearance and VAT.
