የቦንጋ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የ2019 በጀት ዓመት የውስጥ መንገድ ግንባታ ጨረታ (5 ሎቶች፣ በአጠቃላይ 17,001 ሜትር)
የቦንጋ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት በካፋ ዞን የቦንጋ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ለቦንጋ ከተማ ፋ/ጽ/ቤት በፃፈዉ ደብዳቤ መሠረት በ2019 በጀት ዓመት ዉስጥ ለዉስጥ መንገድ ለመስራት በሎት 01 መስቀል አደባባይ ቀጠና 4,520 ሜትር ዉስጥ ለዉስጥ መንገድ ፤በሎት 02 መሀል ከተማ 2,965ሜትር ዉስጥ ለዉስጥ መንገድ ፤በሎት 03 ሸታ ቀጠና 5,165ሜትር ዉስጥ ለዉስጥ መንገድ በሎት 04 /ፐሎት 1/ኮሌጅ ቀጠና 2,170ሜትር ዉስጥ ለዉስጥ መንገድ እንዲሁም በሎት 05/ፐሎት 2/ ኮሌጅ ቀጠና 2,181ሜትር ዉስጥ ለዉስጥ መንገድ ለማሰራት ስለሚፈልግ በዚህ ንግድ ዘርፍ ከተሰማራችሁ ተጫራቾች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ለመሳተፍ የምትፈልጉ አመልካቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባችሁ።
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸዉ ፤
- የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ፤
- ከገቢዎች ባለስልጣን የቲን ተመዝጋቢ የሆነ፣
- ተጫራቾች ደረጃ GC/RC -4 እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት;
- ተጫራቾች የመልካም ስራ አፈጻጸም ደብዳቤ ከሰሩበት መ/ቤትና ከተቆጣጣሪ ቢሮ ማጻፍና ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፁ መረጃዎች በጨረታ ዶክመንት ላይ ያሉት ገዥ ይሆናሉ
- የጨረታው ሰነድ የማይመለስ 1000 /አንድ ሺህ ብር/በአካዉንት ቁጥር 1000705880682 በማስያዝ ከካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይችላል ፤
- የጨረታ ሰነዱ በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ በታሸገ ኢንቨሎፕ ፋይናንሻል ኦሪጂናል ከሁለት ኮፒ ጋር እንዲሁም ቴክኒካል ኦሪጂናል ከሁለት ኮፒ ጋር CPO ለብቻ ተዘጋጅቶ የሚቀርብ ሲሆን ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ22ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መከፈቻ ሰዓት ያለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉለውም፣
- የጨረታ ማስከበሪያ በሎት 01 400,000/አራት መቶ ሺህ ብር/፤በሎት 02፡ 250,000/ሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር/ በሎት03 350,000/ሶስት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር/ በሎት 04 /ፐሎት1/ 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እንዲሁም በሎት 05/ፐሎት2/:200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፣
- የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በፖስታ ታሽጎ የሚገባውም ሆነ የሚከፈተው በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ይሆናል ፤
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 047-331-0807/805 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፤
የቦንጋ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Bonga City Finance Office, Kafa Zone, South West Ethiopia, seeks GC/RC grade 4+ contractors to build internal town roads in five lots (Meskel Square, city centre, Sheta and two College zone sections, about 17 km in total). Bidders need a renewed licence, TIN, VAT and good performance letters.
