የጋምቤላ መምህራን ትምህርትና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለተማሪዎች ቀለብ የጤፍ፣ የጥራጥሬ፣ የፍርኖ ዱቄት፣ የዘይት፣ የስኳርና የሥጋ አቅርቦት
Gambella Teachers Education and Health Science College (የጋምቤላ መምህራን ትምህርትና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጋምቤላ መምህራን ትምህርትና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለመደበኛና የክረምት ኮርስ ተማሪዎች ቀለብ አገልግሎት የሚያስፈልጉ የምግብ ጥሬ እቃዎችን በሎት በተከፋፈለው መሠረት በከፊልም ሆነ በጠቅላላው ሊያቀርቡ የሚችሉ ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት የሚቆይ የኮንትራት ውል ስምምነት በመዋዋል ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
ሎት አንድ፡- ሁለተኛ ደረጃ ጤፍ የተፈጨ፣
ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች መሆን ይጠበቅባቸዋል።
ሎት ሁለት፡- ጥራጥሬዎችና የተለያዩ የምግብ ጥሬ ዕቃዎች፣
ሎት ሦስት፡- ፍርኖ ዱቄት፣ የምግብ ዘይትና ስኳር፣
ሎት አራት፡- የሥጋ አቅርቦት ሆኖ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በዝርዝር የተመለከቱ መሥፈርቶችን የሚያሟሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር ወይም በክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ወይም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡ፣
- የ2018 ዓ.ም ግብር ስለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ስለመኖራቸው ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በማስታወቂያ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከኮሌጁ ግዥና /ፋ/ን/ብ/አስተዳደር ቢሮ ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ 10,000 (አሥር ሺህ ብር) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት አቅርበው በደረሰኝ ማስያዝ ወይም ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች ኮሌጁ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የሚጫረቱበትን ነጠላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጥንቃቄ መሙላት ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
- ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ አድርገው ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒውን ይዞ በመቅረብ በኮሌጁ ግዥና ፋ/ን/ብ/አስ/ቡድን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መጫረት ይችላሉ።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 4:30 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ ግዥና ፋ/ን/ብ/አስ/ቡድን ቢሮ ውስጥ ይከፈታል። በአጋጣሚ 16ኛው ቀን የመንግሥት የሥራ ቀን የማይሆን ከሆነ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልጋቸው በስልክ ቁጥር 0475510293 ወይም በአካል ቀርበው ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ።
- ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የጋምቤላ መምህራን ትምህርትና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
✨ messages.ai_summary
Gambella Teachers Education and Health Science College seeks suppliers of student food items in 4 lots: ground teff, pulses and other food items, flour, edible oil and sugar, and meat, under a one-year contract. Open bid.
