Tender Detail

Tender Details

  • Company የቡሉኮ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር
  • Address ሸገር ከተማ ፣ ፉሪ ክ/ከተማ (ከዓለም ገና ወደ ቡታጅራ መንገድ 1.3 ኪ.ሜ) የቀድሞው አይካ አዲስ ጨርቃጨርቅ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0996672951
  • Website
  • Deadline25 Nov 2026, 10:15 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 1,000.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 20,000.00 (CPO ወይም ያለገደብ የባንክ ዋስትና)
  • opening dateህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም 4:30 ሰዓት
  • Categories Accounting & Auditing , Audit Service

ቡሉኮ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር የሂሳብ ኦዲት አገልግሎት (የሂሳብ መርማሪ) ቅጥር

የቡሉኮ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በግዥ መለያ ቁጥር

(ብ.ግ.ጨ.ቁ BTSC/NCB/Serv/05/2019)

ቡሉኮ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና በግል ባለሃብቶች ሽርክና የተቋቋመ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የልማት ድርጅት ነው:: ድርጅታችን ከ2018 በጀት ዓመት ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ (ኢ.ኢ.አ የ2018፣ የ2019 እና የ2020) የበጀት ዓመታት የሂሳብ መርማሪ (ኦዲተር) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመግባት ለማሠራት ይፈልጋል። በዚህም መሠረት በግልፅ ጨረታው ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መረጃዎች ማሟላትና ማቅረብ አለባቸው::

  1. ከሚመለከተው አካል በዘርፉ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የወሰደና የታደሰ፤
  2. የታደሰ ንግድ ፈቃድና የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
  3. የግብር ከፋይ የምዝገባ ሠርተፍኬት፣
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሠርተፍኬት፣
  5. በጨረታ ለመሳተፍ ግብር ነፃ ስለመሆን አግባብ ካለው የገቢዎች መ/ቤት ደብዳቤ፤
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ በሲፒኦ ወይም የባንክ ያለገደብ ዋስትና (ጋራንቲ) ማቅረብ የሚችል፤
  7. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል በሸገር ከተማ ፉሪ ክ/ከተማ (ኬንተሪ ወደ ቡታጅራ በሚወስደው መንገድ 1.3 ኪ/ሜ ላይ) በድርጅቱ ቅጥር ግቢ የግዥና አቅርቦት መምሪያ ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3:00 እስከ 6:00 ከሰዓት በኋላ ከ7:30 እስከ 10:30 ሰዓት ቅዳሜ ከጠዋቱ 3:00 እስከ 6:00 ሰዓት መግዛት ይቻላል::
  8. ጨረታው ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:15 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት 4:30 ሰዓት ላይ በግልፅ ይከፈታል::
  9. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0946-81-73-02 ደውለው መጠየቅ ይችላል።
  10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።

አድራሻ፡ ኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሸገር ከተማ፣ ፉሪ ክ/ከተማ (ከኬንትሪ ወደ ቡታጅራ መንገድ 1.3 ኪ.ሜ)

ቡሉኮ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር

✨ messages.ai_summary
Buluko Textile S.C., an Oromia regional development enterprise in Sheger City, seeks a licensed external auditor to audit its accounts for three consecutive fiscal years. Open bid.
Save Tender