የድሬዳዋ አስተዳደር መንገድና ትራንስፖርት ሎጅስቲክ ኤጀንሲ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ግዥ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨ/መ/ቁ 0003/19
በድሬዳዋ አስተዳደር የመንገድና ትራንስፖርት ሎጅስቲክ ኤጀንሲ በ2019ዓ.ም በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
በዚሁ መሰረት:-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው::
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
- በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ::
- ተጫራቶች የጨረታ ሠነዱን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሠነዱን በመንገድና ትራንስፖርት ሎጅስቲክ ኤጀንሲ ቢሮ ቁጥር 6 ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል መግዛት የሚችሉ ሲሆን በጨረታ መክፈቻው እለት የጨረታ ሠነዱን በትክክል ሞልተው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዋናውንና ኮፒውን በአግባቡ አሽገው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል::
- የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሠዓት ላይ ታሽጎ በዛው ዕለት 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 6 በግልጽ ይከፈታል፤ ቀኑ በዓል ወይም የዕረፍት ቀናት ላይ ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን::
- ተጫራቾች ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይንም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ቢያስፈልግ በሚከተለው አድራሻ መጠቀም ይችላሉ:- በድሬዳዋ አስተዳደር የመንገድና ትራንስፖርት ሎጅስቲክ ባለስልጣን
ቢሮ ቁጥር 6
የስልክ ቁጥር:- 0942279841
በድሬዳዋ አስተዳደር የመንገድና ትራንስፖርት ሎጅስቲክ ኤጀንሲ
✨ messages.ai_summary
Dire Dawa Administration Road and Transport Logistics Agency seeks suppliers of various vehicles for office use. Bidders need a renewed trade licence, VAT registration and supplier registration. Open bid.
