Tender Detail

Tender Details


መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንገድ ቅየሳ መሳሪያ፣ የድሮን ካሜራ፣ የብሎኬት ማምረቻ ማሽን እና የሞተር ሳይክል ግዥ

መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት የመንገድ ቅየሳ መሳሪያ/ማሽን፣ ለኢንተርፕራይዞች ጽ/ቤት የብሎኬት ማምረቻ ማሽን፣ ለመንግስት ኮምንኬሽን ጽ/ቤት ለቀረጻ የሚሆን የድሮን ካሜራ እና ለፖሊስ ጽ/ት የእጀባ ትራፊክ ሞተር ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

  1. ሎት አንድ የመንገድ ቅየሳ መሳሪያ/ማሽን ግዥ ጨረታ
  2. ሎት ሁለት ኤሌክትሮኒክስ እና ለቀረጻ የሚሆን የድሮን ካሜራ ዕቃዎች ግዥ ጨረታ
  3. ሎት ሶስት የብሎኬት ማምረቻ ማሽን ግዥ ጨረታ
  4. ሎት አራት የሞተር ሳይክል ግዥ ጨረታ

በዚህም መሠረት ከታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን::

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው/ላት፣
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ላት፣
  3. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ላት፤
  4. የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል፤
  5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያለው/ላት፣
  6. ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆነ/ነች፤
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ/ ብር በጥሬ ብር ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ በመሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ስም በማሰራት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል::
  8. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-7 የተጠቀሱ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ዋና እና ኮፒውን በማዘጋጀት በጥንቃቄ በታሸገ በሁለት ወጥ ፖስታዎች ለየብቻው በማዘጋጀት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  9. ሁሉም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ እንደተመለከተው ለሚጫረቱት ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ማቅረብ አለባቸው:: ዘግይቶ የቀረበ ጨረታ ውድቅ ይደረጋል:: ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በ15ኛው ቀን ሎት አንድ በ3:00 ሰዓት ታሽጎ 3:30 ላይ ይከፈታል ሎት ሁለት በ4:30 ሰዓት ታሽጎ 5:00 ላይ ይከፈታል ሎት ሶስት በ8:00 ሰዓት ታሽጎ 8:30 ላይ ይከፈታል እና ሎት አራት በ9:30 ሰዓት ታሽጎ 10:00 ላይ ይከፈታል:: የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል::
  10. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶችን የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይችላል።
  11. ጨረታ አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርበውን ዕቃ ወይም ንብረት በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቀርቦ ማስረከብ ይኖርበታል::
  12. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-11 ድረስ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን፣ ማስረጃዎችን እና ሁኔታዎችን ማሟላት ይኖርባቸዋል:: የተጠቀሱትን መስፈርቶችን እንዲያቀርቡ የተጠየቁ ማስረጃዎችን ያላቀረበ እንደሆነ ይህንን ባለማድረጉ ምክንያት ከውድድር ውጭ ይደረጋል::

ማሳሰቢያ

  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  • ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥሮችን 0916767044 ወይም 0910409544 ይደውሉ::

የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Melo Koza Woreda Finance Office (Gofa Zone, South Ethiopia) seeks suppliers in 4 lots: road survey equipment, a drone camera and electronics, a concrete block-making machine, and a traffic escort motorcycle. Open bid.
Save Tender

Dashen Bank – Building Management System Upgrade, Electric Motorcycles, Tablets and IBM Storage Lice...

READ MORE
Ethiopian Press Agency – Supply of Printing Machinery from Pre-Press to Post-Press (Re-Bid, ICB)

READ MORE
Oromia Pipe Factory PLC – Supply, Installation and Commissioning of HDPE and uPVC Pipe Testing Machi...

READ MORE