ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አ/ማ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን መለዋወጫ እቃዎች የአዉቶቢስ ጎማና ባትሪዎች፣ የሞተር፣የጊርቦክስና ዲፈረንሽያል ዘይት እና አዉቶሞቢል መኪኖችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ሎት 1 የዩቶንግ አዉቶቢስ መለዋወጫ ዕቃዎች ሎት 2. የሞተር፣የጊርቦክስና ዲፈረንሽያል ዘይት ሎት 3. የአዉቶቢስ ጎማና ባትሪዎች ሎት 4. አዉቶሞቢል መኪኖችን
Selam Bus Line Share Company (ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አ/ማ)
ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አክስዮን ማህበር
SELAM BUS LINE SHARE COMPANY
የጨረታ ማስታወቂያ
ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አ/ማ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን መለዋወጫ እቃዎች የአዉቶቢስ ጎማና ባትሪዎች፣ የሞተር፣የጊርቦክስና ዲፈረንሽያል ዘይት እና አዉቶሞቢል መኪኖችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የዩቶንግ አዉቶቢስ መለዋወጫ ዕቃዎች
- ሎት 2. የሞተር፣የጊርቦክስና ዲፈረንሽያል ዘይት
- ሎት 3. የአዉቶቢስ ጎማና ባትሪዎች
- ሎት 4. አዉቶሞቢል መኪኖችን
ስለሆነም:- አ/ማህበሩ ከላይ ከሎት 1 እስከ 4 የተገለፁትን ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ በጨረታው መወዳደር ለሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች በተገለፀዉ የጨረታ መመሪያ መሠረት መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የምዝገባ የምስክር ወረቀት ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ክሊራንስ የተሰጣቸው፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት እና TIN ቲን ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ዘወትር ከ2:30-11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ 2:30-6:30 ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ በአ/ማህበሩ ዋና መ/ቤት መስቀል አደባባይ ፊንፊኔ ህንፃ 6ተኛ ፎቅ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ንብረት የጨረታ ማስከበሪያ (bid bond) ለሚያቀርቡትን እቃ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) በባንክ የክፍያ ማዘዣ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በሰላም የህዝብ ማመላለሻ አ/ማ (Selam bus line share company) ስም አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ በድርጅቱ ጋራዥ ዉስጥ ለዚሁ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታዉ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ9:15 በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- ማንኛዉም ተጫራች የሚጫረትባቸዉን ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ (specification) ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ፕሮፖዛሎች በግልፅ በመጥቀስ ለየብቻ በማዘጋጀትና በማሸግ በተጨማሪ ሁለቱንም በአንድ ኢንቨሎፕ በማሸግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸዉ።
- ከሎት3፣ሎት4 እና ከመስታወቶች በስተቀር ለሁሉም እቃዎች ናሙና (sampel) ጨረታዉ ከመዘጋቱ ከአንድ ቀን በፊት ቀድመው የሩፋኤ ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘዉ የድርጅቱ መጋዘን ማስገባት አለባቸዉ ናሙና ያልቀረበባቸዉ እቃዎች በጨረታዉ እንዳልቀረቡ ተቆጥሮ ዉድቅ ይደረጋሉ ወይም ፋይናንሽያል ዉጤታቸዉ አይታይም።
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸዉ ከተነገራቸዉ ወይም የአሸናፊነት ደብዳቤ ከተላከላቸዉ ቀን ጀምሮ በ15 (በአስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናቶች ዉስጥ በራሳቸዉ ትራንስፖርት በማጓጓዝ ያሸነፉትን ንብረት ሙሉ በሙሉ በገቹዉ ድርጅት ቅጥር ግቢ ዉስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
ለተጨማሪ መረጃ :- በስልክ ቁጥር 09-75-23-27-10 // 011-515-86-96 ደዉለዉ ይጠይቁ።
ሰላም የሕዝብ ማመላለሻ አ.ማ
✨ messages.ai_summary
Selam Bus Line Share Company buys by open tender in four lots: Yutong bus spare parts (Lot 1), engine, gearbox and differential oil (Lot 2), bus tyres and batteries (Lot 3) and automobiles (Lot 4). Bidders need a renewed trade licence, registration, tax clearance, VAT and TIN.
