Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa City Administration Investment Commission (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን)
  • Address ልደታ ክፍለ ከተማ ሜክሲኮ ዮቤክ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 በግዢ፤ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5-57-78-46
  • Websitehttps://investaddisababa.com/
  • Deadline17 Nov 2026, 8:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ለሎት 1፡- ለሁለቱም 30,000 (ሰላሳ ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) የባንክ ዋስትና ከቴክኒክ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  • opening dateጨረታው በ11ኛው ቀን ጠዋት 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል።
  • Categories Consultancy Service , Research Consultant , Study And Research And Tools

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት ሁለት የጥናትና ምርምር ሥራዎችን (Investment Priorities, Opportunities and Future Directions፤ Stakeholder Integration and Investment Growth) በግልጽ ጨረታ ከብቁ አማካሪዎች ጋር ያወዳድሮ ማስጠናት ይፈልጋል።

Addis Ababa City Administration Investment Commission (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን)


ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 003/2019

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኮሚሽኑን ራዕይ እና ተልዕኮ ማሳካት የሚያስችሉ -ሎት 1- ሁለት (2) የተለያዩ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን፣-

  • በአዲስ አበባ ከተማ ቀዳሚ የኢንቨስትመንት አማራጮች፣ እድሎችና የወደፊት አቅጣጫዎች (Investment priorities, opportunities, and future Directions in Addis Ababa)
  • በአዲስ አበባ ከተማ የባለድርሻ አካላት ትስስር እና የኢንቨስትመንት እድገት (The integration of stakeholders and the growth of investment in Addis Ababa City) በ2019 በጀት ዓመት በውጭ አቅም (Consultants) በዘርፉ የተሰማሩና ብቁ የሆኑ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስጠናት አስፈልጓል።

ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ህጋዊ እና አውቅና ማረጋገጫ መስፈርቶች:-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት።
  2. በግዥና ንብረት ባለሥልጣን የዕቃዎችና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

ለጥናቱ ሥራ የተቀመጡ ልዩ የብቃት መመዘኛዎች፣

  • የሥራ ልምድ፣- ጥናቱ የሚያጠኑ አካላት በማስተርስ ዲግሪ ቢያንስ 6 ዓመት በፒኤችዲ 5 ዓመት አጠቃላይ በጥናት ስራና ተዛማጅ ስራዎች ላይ ልምድ ያላቸው፣ 3 ተመሳሳይ የጥናት ፕሮጀክቶችን በተሳካ ሁኔታ ያጠናቀቁ ለተሰሩ ስራዎች መረጃ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።
  • የትምህርት (ዝግጅት እና ዓይነት) ለጥናት ሥራው የተሰማሩት ባለሙያዎች ሥራውን ለመሥራት የሚያስችል ተገቢና ተዛማጅ የሆነ ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅት (እውቅና ካለው የትምህርት ተቋም በሚኒጅመንት፣ በኢኮኖሚክስ፣ በልማት ጥናት፣ ወይም በተመሳሳይ ተያያዥ መስኮች ቢያንስ የማስተርስ ዲግሪ ወይም ፒኤችዲ ያለው/ላት) ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ።
  • ለጥናቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን መረጃዎችን ታማኝ ከሆኑ የመንግሥት ተቋማት እና አስተማማኝ ምንጮች ብቻ ተጠቅሞ የመሥራት ግዴታ አለበት።
  • እያንዳንዱን የጥናት ሥራ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች (በትርጉም) ማዘጋጀት የሚችል።
  • እያንዳንዱን የጥናት የሥራ ውል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ በ4 (አራት) ወራት ጊዜ ውስጥ አጠናቆ በሃርድ ኮፒ (Hard Copy) እና በሶፍት ኮፒ (Soft Copy) ማስረከብ የሚችል።

የጨረታ አቀራረብ እና መመሪያዎች፣-

  1. ተጫራቾች የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) የኢትዮጵያ ብር በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ሜክሲኮ ሰንጋተራ የቤክ ኮሜርሻል ሴንተር 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 በግዥ፣ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ለሎት 1፡- ለሁለቱም 30,000 (ሰላሳ ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) የባንክ ዋስትና ከቴክኒክ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አሥር) ተከታታይ የሥራ ቀናት (ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:30 እስከ ከቀኑ 11:00) ክፍት ሆኖ ይቆያል።
  4. የቴክኒክ ብቃት (የመጀመሪያዎቹ 5 መስፈርቶችና የንግድ ፈቃድ ማስረጃዎች ) እና የፋይናንስ የዋጋ አቅርቦት በተለያዩ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ መቅረብ ይኖርበታል።
  5. ጨረታው በ11ኛው ቀን ጠዋት 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ሜክሲኮ ሰንጋተራ የቤክ ኮሜርሻል ሴንተር 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 በግዥ፣ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ይከፈታል። (የመዝጊያ እና መክፈቻው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚዘጋ እና የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን)።
  6. አሸናፊው ተጫራች ውል ከመፈረሙ በፊት የውል ማስከበሪያ ማቅረብ ይኖርበታል።
  7. አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነቱ በተገለፀበት ከ05 /አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 % የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ07/ሰባት ቀናት ውስጥ ውል መያዝ የሚችል መሆን አለበት፣
  8. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የሰጠውን ዋጋ ለማሻሻል፣ ለመለወጥ ወይም ትቼዋለሁ ማለት አይችልም፣
  10. ማንኛውም ተጫራች ማጭበርበር ወይም ሙስናን በተመለከተ በኢትዮጵያ ህጎች የተደነገገውን የሚያከብር መሆኑን ይገባዋል፣
  11. ጨረታውን ለማዛባት ሙከራ የሚያደርግ ተጫራች ከጨረታው እንደሚሰረዝ እና ወደፊትም

ማሳሰቢያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ሜክሲኮ ሰንጋተራ የቤክ ኮሜርሻል ሴንተር 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 በግዥ፣ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መረጃ ማግኘት ይቻላል።

ለተጨማሪ መረጃም በስልክ ቁጥር 0115-5778-46 ደውሎ ማናገር ይቻላል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

✨ messages.ai_summary
Addis Ababa City Administration Investment Commission seeks qualified consultants for two research studies: investment priorities, opportunities and future directions in Addis Ababa, and stakeholder integration and investment growth. Requires master's/PhD experts with relevant experience.
Save Tender

Oromia Bank – Main Consultant for Design and Supervision of High-Rise Headquarters Building (Express...

READ MORE
Hibret Insurance – Consultancy for Corporate Strategic Plan and Organizational Structure, Job Evalua...

READ MORE