የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የዕቅድ ማስፈፀሚያ የሚውሉ የመኪና ጎማና እቃዎች፣ የአትክልት ዘር፣ የእንስሳት መድሀኒት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ የኮምፒውተር ጥገና፣ የዶሮና የንብ ርባታ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ያወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ግዥ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር:-ጉ/ክ/ከ/ዋ/ስ/አስ/ፋ/ 002/2019 ዓ.ም
በጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የዕቅድ ማስፈፀሚያ የሚውሉ የጨረታ ማስታወቂያ፣ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1. የተለያዩ የመኪና ጎማና እቃዎች
- ሎት 2. የተለያዩ የአትክልት ዘሮች
- ሎት 3. የተለያዩ የእንስሳት መድሀኒት
- ሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት 5. የደንብ ልብስ ስፌት ለ2ኛ ጊዜ
- ሎት 6. የእ.ቅ.ቢ. ህግ የችሎት ልብስ ሱፍ ጨርቅ በገበር የተሰፋ እና የሰራተኛ ደንብ ልብስ ለ2ኛ ጊዜ
- ሎት 7. የኮምፒውተር ጥገና
- ሎት 8. እንቁላል ጣይቁብ ዶሮ፣ የቁብ ዶሮ መኖ፣ ባለ50 ስታንዳርዱን የጠበቀ ኬጅ
- ሎት 9. የንብ መንጋ፣ ዘመናዊ የንብ ቀፎ
- ሎት 10. የሰም ማተሚያ፣ ማር ማጣሪያ
ስለዚህ በዚሁ የስራ ዘርፍ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች:-
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ሎት1. 20,000.00 ብር ፣ ሎት2. 10,000.00 ብር ፣ ሎት3. 10,000.00 ብር ፣ ሎት4. 25,000.00 ብር ፣ ሎት5.10,000.00 ብር ፣ሎት6. 30,000.00 ብር ፣ ሎት7. 10,000.00 ብር ፣ ሎት8. 30,000.00 ብር ፣ ሎት9. 20,000.00 ብር ፣ሎት10. 20,000.00 ብር የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀው ዝርዝር ጉዳዮችና የተጫራቾችን መመሪያ የያዘ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመግዛት 9ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ።
- ጨረታው መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀን ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 4 ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው የሚታሸግበት ቀን በ10ኛ ቀን 11:30 ሰዓት ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ11ኛው ቀን 4:30 ሰዓት ይከፈታል። የሚከፈትበት ቦታ 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4።
- ናሙና መቅረብ ባለባቸው እቃዎች ላይ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል ህጋዊ ወኪል ለመሆናችሁ የሚገልጽ ደብዳቤ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ፣ ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው። እያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማህተብ ማድረግ አለበት። /VAT/ ያካተተ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መጥቀስ ይኖርበታል ካልተጠቀሰ እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
- ኦርጅናል እና ኮፒውን ሰነድ ለየብቻ አድርጎ በማያያዝ ማስገባት ይኖርበታል።
- በጨረታው ላይ የእቃውን ብዛት 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይቻላል።
- በውሉ ላይ 25% መጨመር ይቻላል።
- ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ግዴታ ነው ከተከፈተ እና የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ ናሙና የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ:-
አድራሻ:- አዲሱ ገበያ ኖክ ጀርባ የጉ/ክ/ከተማ አዲሱ ህንጻ 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 04 በስልክ ቁጥር:- 0921770036 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ማሳሰቢያ:- ሁሉንም እቃዎች በተፈለገበት ቀንና ቦታ በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
በጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Gulele Sub-City Chief Executive Administration and Finance Office, Addis Ababa, buys in 10 lots: tyres, vegetable seeds, veterinary drugs, electronics, uniform sewing, court robes, computer repair, laying hens with feed and cages, bee colonies and hives, wax press and honey strainer.
