የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለገበ 3 እና ገበ 2 ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች የቤት ዕቃዎች፣ ፍሪጆች፣ መጋረጃዎችና የክሊኒክ ዕቃዎች ግዥ (በድጋሚ የወጣ)
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEP/GBP/NCB/05/2019
- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለገበ 3 እና ገበ 2 ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች በሎት-1 የመኝታ ቤት፣የሳሎን እና የምግብ ቤት ዕቃዎች፣ በሎት-2 ፍሪጅች እና የመስኮት መጋረጃዎች ፣ በሎት-3 የምግብ ቤት እና የልብስ ማጠቢያ ዕቃዎች ፣ በሎት-4 የውሃ ማሞቂያ እና የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ዕቃዎች እና በሎት-5 የመከላከያ ክሊኒክ ዕቃዎች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል:: ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ::
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ሰዓት ከተክለ ብርሀን አምባዬ ኮንስትራክሽን ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሰሜን ኃይልና ፋይናንስ አስተዳደር ህንጻ 2ኛ ፎቅ ከግዥ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ህይል ህንጻ 2ኛ ፎቅ ከፋይናንስ ቢዝነስ ግዥ ቢሮ ቁጥር 114 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን የሎት ዕቃዎች በሚመለከት የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ዝርዝር በታሸገ ፖስታ የጨረታ ቁጥር EEP/GBP/NCB/05/2019 የሚል ምልክት በማድረግ 1(አንድ) ኦሪጂናል እና 2 (ሁለት) ኮፒ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ከዚህ በታች በተገለጸው ሰንጠረዥ መሰረት ለ90 / ዘጠና/ ቀን የአገልግሎት ጊዜ የሚቆይ የባንክ ክፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power) ስም የተዘጋጀ ማቅረብ አለባቸው::
የሎት ቁጥር የግዥው ዓይነት የጨረታው ማስከበሪያ መጠን /በብር/ ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ሎት-1 የመኝታ ቤት፣የሳሎን እና የምግብ ቤት ዕቃዎች ግዥ ብር 800,000.00 ህዳር 28 ቀን 2019 ዓ.ም በ8:00 ሰዓት ህዳር 28 ቀን 2019 ዓ.ም በ8:30 ሰዓት ሎት-2 ፍሪጆች እና የመስኮት መጋረጃዎች ግዥ ብር 400,000,00 ሎት 3 የምግብ ቤት እና የልብስ ማጠቢያ ዕቃዎች ግዥ ብር 600,000.00 ሎት 4 የውሃ ማሞቂያ እና የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ዕቃዎች ግዥ ብር 100,000.00 ሎት 5 የመከላከያ ክሊኒክ ዕቃዎች ግዥ ብር 100,000.00 - ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-5 57 40 11 መደወል ይችላሉ ::
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Electric Power seeks suppliers for two of its power stations in 5 lots: bedroom, living and dining furniture; fridges and window curtains; kitchen and laundry items; water heaters and waste bins; and clinic items. Licensed, VAT-registered suppliers on the government supplier list. Rebid.
