Tender Detail

Tender Details

  • Company የሐረሪ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለስልጣን
  • Address ሐረር ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0910415925
  • Website
  • Deadline19 Nov 2026, 9:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 1,500.00
  • Bid SecurityCPO 5%
  • opening dateህዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት፣ ቢሮ 4ኛ ፎቅ አዳራሽ
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

የሐረሪ ክልል የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን የጀጎል ሞዴል መንደር የመኖሪያ፣ የንግድና የካፌ ቦታዎች የሊዝ ጨረታ (10ኛ ዙር፣ የጊዜ ማራዘሚያ)

የሐረሪ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለስልጣን


የ10ኛ ዙር የጀጎል ሞዴል መንደር የሊዝ ጨረታ ጊዜን ማራዘም ማስታወቂያ

የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን በሐረር ከተማ ጀጎል አባድር ፕላዛ አካባቢ (የጀጎል ሞዴል መንደር) ለመኖሪያ (63 ፓርስሎች) ለንግድ መደብሮች (31 ፓርስሎች) እና ለካፌ ንግድ (1 ፓርሰል) በጠቅላላው 95 ፓርስሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም. ጨረታ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል። ሆኖም ተወዳዳሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉና ሰፊ የምዝገባ እድል ለመስጠት ሲባል የጨረታ ሰነድ መግዣ መመለሻና መከፈቻ ጊዜ ለተጨማሪ 10 የሥራ ቀናት ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

በዚሁ መሠረት:- የሰነድ ሽያጭና ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን:- እስከ ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ድረስ ተራዝሟል። የጨረታ ሳጥን የሚዘጋበት ጊዜ:- ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ይሆናል::

የጨረታ ሳጥን የሚከፈትበት ጊዜ:- ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ 4ኛ ፎቅ አዳራሽ ይከናወናል::

የሰነድ መግዣ አማራጮች:- በኦንላይን ፖርታል https://sltms.hararsmartlandsystem.gov.et በመግባት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000017606364 ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ በማያያዝ ወይም በአካል በመቅረብ በመሶብ 1 ማዕከል እንዲሁም በዋናው መሥሪያ ቤታችን ምድር ቤት ቢሮ ቁጥር 49 መግዛት ይቻላል። ከዚህ ቀደም በጨረታ ማስታወቂያው ላይ የወጡት የCPO መጠን (5%) አነስተኛ የቅድመ ክፍያ መጠን (20%) የሰነድ ዋጋ (1,500.00 ብር) እና የማወዳደሪያ መስፈርቶች (80/20) እንደተጠበቁ ናቸው።

ለተጨማሪ መረጃ በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ይፋዊ ድረ-ገፅ https://hudco.gov.et በመግባት ወይም በአካል ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል።

በሐ/ሕ/ክ/መ/ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ
የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን

✨ messages.ai_summary
The Harari Region Land Development and Management Authority has extended its 10th-round lease auction of 95 plots at the Jegol Model Village, Abadir Plaza, Harar: 63 residential, 31 commercial and 1 café plot. Documents online or in person. Lease auction (deadline extended).
Save Tender