በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ማዕከል የ1ኛ ደረጃ የስንዴ ዱቄት ግዥ
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት ማዕከል
የስንዴ ዱቄት ግዥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ማዕከል በ2019 በጀት ዘመን በእርምት ላይ ለሚገኙ ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውል 1ኛ ደረጃ የስንዴ ዱቄትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለዚህ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር400.00 (አራት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነዱን ዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት ማዕከል ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 32 ከግዥ ከንውን ቡድን ክፍል በመግዛት በጨረታው ሰነድ ላይ የምትሸጡበትን ዋጋ በመግለፅ በታሸገ ኤንቨሎፕ በመሙላት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን 4:00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- የጨረታው ሳጥን መዝጊያ በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ይዘጋል::
- የጨረታ ሳጥን መከፈቻ 10ኛው ቀን 4:30 ሰዓት ይሆናል::
- የተገለፀው የመዝጊያና መከፈቻ ቀን ካላንደር የሚዘጋው ወይም የስራ ቀን ሆኖ ከተገኘ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል::
- ለመወዳደር የሚመጡ ተጫራቾች:-
- የጨረታ ማስከበሪያ በፌዴራል የመንግስት ግዥ አፈፃፀም መመሪያ 1073/2017 አንቀፅ 116 ንዑ.አ. (6) መሰረት ተመጣጣኝ የሆነ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ከኦርጅናል ጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- አግባብነት ያለው የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርበታል::
- የዘመኑን የመንግስት ግብር ግዴታ መወጣታቸውን የሚገልፅ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል::
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች) ማቅረብ ይኖርበታል::
- በግዥ ኤጀንሲ ድረ-ገፅ (WWW.ppa.gov.et) በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን ይኖርበታል::
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል::
- ናሙና የተጠየቀባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ግዴታ መሆኑን በማወቅ ዋጋ ተሞልቶ ናሙና አለማቅረብ የተከለከለ ነው::
- ለሚጫረቱት እቃ በዘርፉ የተመገቡ መሆን አለባቸው::
- ከላይ እንደተገለፀው ጨረታው በማዕከሉ ቅጥር ግቢ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 32 ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለ ጠመረጃ:- በስልክ ቁጥር 0464414301 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ማዕከል /ዝዋይ/
✨ messages.ai_summary
The Federal Prison Commission Ziway Rehabilitation and Development Correctional Centre seeks suppliers of first-grade wheat flour for inmate meals. Bidders need a renewed licence, tax clearance letter, VAT certificate where required and PPA supplier registration. Open bid.
