Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline08 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋ 1/4 ብር 1,039,362.50 (C.P.O በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
  • opening dateምዝገባው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ፣ የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የሚገኝ ቤትና ይዞታ የሐራጅ ሽያጭ (በድጋሚ የወጣ)

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍባለሙብት እነ ጌታቸው ቦጋለ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ቦጋለ ማናዬ ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.152115 በቀን 19/07/2017ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ እና በኮ/መ/ቁ.168745 በቀን 12/10/2017ዓ.ም በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ፍርድ ያረፈበት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቤ.ቁ.4334 የሆነ የይዞታ ስፋት 296 ካ/ሜ የካርታ ቁጥርቦሌ/13/44/4/6/8093/52884/01 ከሆነው ይዞታ ነባር ይዞታውን 150ካ/ሜ እና በይዞታው 65 ካ/ሜ ስፋት ላይ ያረፈውን አራት ክፍሎች ያሉት ቤት እንዲሁም ከቤቱ ጋር ተያይዘው የተሰሩት በ13 ካ/ሜ ይዞታ ላይ የወጣ 1( አንድ) ክፍል የብሎኬት እና 5 ካ/ሜ ላይ ያረፈውን 1 (አንድ) የጭቃ ቤት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 4,157,450 ( አራት ሚሊዮን አንድ መቶ ሃምሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ሃምሳ ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ታህሳስ 14 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል:: ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.168745 በቀን 12/02/2019 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በድጋሚ ሐራጅ ጨረታ ሆኖ 1/4ኛ ብር 1,039,362.50 ( አንድ ሚሊዮን ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ ሶስት መቶ ስልሳ ሁለት ከ50/100) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ከህዳር 29 ቀን 2019ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል::የተጫራቾች ምዝገባ 4:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል::

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለሙብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለሙብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት ¼ ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል:: ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም:: በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Federal Courts Judgment Execution Office re-auctions, by court order, a house property in Bole sub-city, Woreda 13, Addis Ababa: a 296 m² titled plot with a four-room house plus a block room and a mud house. The buyer pays transaction tax; site visits by arrangement. Second-round public auction.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender