Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ጂምናስቲክስ ፌዴሬሽን
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline09 Nov 2026, 4:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price5000(አምስት ሺህ ብር)
  • Bid Securityእያንዳንዱ ተጫራች ብር 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበርያ ሲፒኦ በፌዴሬሽኑ ስም ማቅረብ ይኖርበታል።
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Advertising And Promotion , Consultancy Service , Marketing

የኢትዮጵያ ጂምናስቲክስ ፌዴሬሽን የጂምናስቲክስ ስፖርትን ለማሳደግ፣ የገቢ ምንጮቹን ለማስፋት እና ዘላቂ የግል ዘርፍ አጋርነቶችን ለመፍጠር የማርኬቲንግ፣ የስፖንሰርሺፕ እና ኮሚዩኒኬሽን ስትራቴጂ፣ የግብይት እቅድ ማውጣት፣ እና የገቢ ማሰባሰብ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል ማንኛውንም ብቁ የማርኬቲንግ/ ስፖንሰርሺፕ አፈላላጊ እና አማካሪ ኤጀንሲ ወይም አገልግሎት ሰጪ እንዲወዳደር ይጋብዛል።

የኢትዮጵያ ጂምናስቲክስ ፌዴሬሽን


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር:- 002/2019

የኢትዮጵያ ጂምናስቲክስ ፌዴሬሽን የጂምናስቲክስ ስፖርትን ለማሳደግ፣ የገቢ ምንጮቹን ለማስፋት እና ዘላቂ የግል ዘርፍ አጋርነቶችን ለመፍጠር የማርኬቲንግ፣ የስፖንሰርሺፕ እና ኮሚዩኒኬሽን ስትራቴጂ፣ የግብይት እቅድ ማውጣት፣ እና የገቢ ማሰባሰብ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል ማንኛውንም ብቁ የማርኬቲንግ/ ስፖንሰርሺፕ አፈላላጊ እና አማካሪ ኤጀንሲ ወይም አገልግሎት ሰጪ እንዲወዳደር ይጋብዛል።

የስራው ዝርዝር:- የፌዴሬሽኑን የአሁኑን የግብይት ሁኔታ፣ ውድድሮችና የአጋርነት እድሎች መገምገም፣ የስፖንሰርሺፕ እና የማርኬቲንግ ስትራቴጂ ማውጣት፣ የዋጋ ደረጃዎች፣ የስፖንሰር ጥቅል እና የዓመት የግብይት እቅድ ማዘጋጀት፣ የማርኬቲንግ እና ኮሚዩኒኬሽን እቅድ አውጥቶ ማማከር እና መተግበር፣ የሚመለከታቸውን ድርጅቶች መለየት፣ ድርድርን መደገፍ እና የስፖንሰር ግንኙነትን ማስተዳደር፣ በየሩብ ዓመቱ የሥራ እንቅስቃሴ፣ የቀረቡ ሀሳቦች፣ ገቢ የተደረገ ገንዘብ እና የተፈጸሙ ግዴታዎች ሪፖርት ማቅረብን የሚያካትት ይሆናል።

በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች

  • በሕጋዊ ሁኔታ የተመዘገበ ድርጅት መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  • ተገቢ የንግድ ፈቃድና የግብር ምዝገባ ማቅረብ የሚችል፣
  • ለፌዴሬሽኑ የሚያስገባውን ገቢ ጠቅሶ ማስገባት የሚችል፣ እያንዳንዱ ተጫራች ብር 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበርያ ሲፒኦ በፌዴሬሽኑ ስም ማቅረብ ይኖርበታል።
  • የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ ኮንትራት እንደተፈራረመ፣ ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በፌዴሬሽኑ አካውንት ማስያዣ ቅድሚያ ገቢ ማድረግ አለበት።
  • የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት ስድስት ኪሎ በሚገኘው ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር 4ኛ ፎቅ በጽ/ቤት በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
  • ፌዴሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትንና ተያያዥ ሰነዶችን በሙሉ አያይዘው እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ።

የጨረታው መወዳደርያ ቀነ ገደብ፣ ጨረታው ከወጣ በኋላ ባሉት 5 /አምስት/ ቀናት ውስጥ ይሆናል።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር:- 0911-46-80-91/ 0973-19-99-91 ወይም 0910-36-86-80 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ጂምናስቲክስ ፌዴሬሽን

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Gymnastics Federation re-advertises for a marketing and sponsorship agency to prepare its marketing, sponsorship and communication strategy, find and manage sponsors and raise revenue. Open to legally registered firms with a trade licence and tax registration.
Not stated in the notice: opening date. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender

Hibir Construction Corporation invites bids for construction works on Ethiopian Roads Administration...

READ MORE
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ለሚያስገነባው እና ለሚያሳድሰው የግንባታ ስራ በጥቃቅንና አነስተኛ ልዩ አማካሪ ደረጃ 1 ማህበር...

READ MORE