ዓባይ የሕትመትና የወረቀት ፓኬጂንግ ፋብሪካ ለፋብሪካው የሕትመት ሥራዎች አገልግሎት የሚውል 250 ግራም ድብል ኮትድ አርት ወረቀት (250 GSM Double Coated Art Paper) በሁለት የስፋት መጠኖች 61 ሴ.ሜ × 86 ሴ.ሜ እና 70 ሴ.ሜ × 100 ሴ.ሜ በዘርፉ ከተሰማሩና ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸው ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Abay Printing & Paper Packaging PLC
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር አሕየወፓ-02/02/2019
ዓባይ የሕትመትና የወረቀት ፓኬጂንግ ፋብሪካ ለፋብሪካው የሕትመት ሥራዎች አገልግሎት የሚውል 250 GSM wood free both side Coated Art Paper (C2S) በሁለት የስፋት መጠኖች 61 ሴ.ሜ × 86 ሴ.ሜ እና 70 ሴ.ሜ × 100 ሴ.ሜ በዘርፉ ከተሰማሩና ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸው ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታዉ እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የፀና የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸዉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸዉ
- 200,000.00(ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለክታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ፤የተጫራቾች መመሪያ፤የዉል ረቂቅ፤የዋጋ መሙያ ፎርምና ቴክኒክ መግለጫ ያያዘዉን የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዓባይ ሕትመትና የወረቀት ፓኬጂንግ ኃ/የተ/የግ/ማ ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ኢንዱስትሪ መንደር ከጣና ሞባይል አከባቢ ከሚገኘዉ ከፋብሪካዉ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ወይም አዲስ አበባ 4 ኪሎ አማራ ልማት ማህበር አዲሱ ሀንፃ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 219 ከሚገኘዉ ከፋብሪካዉ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ጽ/ቤት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000281546078 ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን የባንክ ደረሰኝ በማቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ተጨማሪ እሴት ታከስን ጨምሮ የጠቅላላ ዋጋዉን 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማያያዝ በታሸገ ፖስታ አድረገዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ስሌት መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከ500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠኑ ከ500,000.00 ብር ብቻ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማስገባት፣ “ዋና (Original)” እና “ኮፒ (Copy)” በሚል በግልጽ ለይቶ በማመልከት፣ በፋብሪካው ግዥና ሎጅስቲክስ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ እስከ ህዳር 07 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በመደበኛ የሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርበታል። የጨረታ ሰነዱ ዋናና ኮፒ በተለያዩ ፖስታዎች ታሽገው በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ መቀመጥ እና በግልጽ መለየት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ እና የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታዉ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ እስከ 60 (ስልሳ) ቀናት ድረስ ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡እንዲሁም የጨረታ ዋጋ በዉል ዘመኑ በሙሉ የፀና መሆን አለበት፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታክስ እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋ ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
- የቴክኒክ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋብሪካው ግቢ በሚገኘው የግዥና ሎጅስቲክስ መምሪያ ህዳር 07 ቀን 2019 ዓ.ም. ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። የፋይናንስ ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በተለየ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከናወናል።ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከፋብሪካዉ ግዥና ሎጅስቲክስ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 0583218865/0942050954/0911709727 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
ዓባይ ሕትመትና የወረቀት ፓኬጂንግ ኃ/የተ/የግ/ማህ ባህር ዳር
