Tender Detail

Tender Details

  • Company ሐካማዝ ኮስሞቲክስና ፕላስቲክ ማምረቻ ኃላ.የተ.የግ ማህበር
  • Address , Phone: +251955332977/913567246
  • Website
  • Deadline06 Nov 2026, 5:00 PM
  • magazineThe Reporter
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Customs clearing service , Freight Transport

የጉምሩክ አስተላላፊነትና የማጓጓዝ (Transit/Freight Forwarding) አገልግሎት - ሐካማዝ ኮስሞቲክስና ፕላስቲክ ማምረቻ ኃ.የተ.የግ.ማ

ሐካማዝ ኮስሞቲክስና ፕላስቲክ ማምረቻ ኃላ.የተ.የግ ማህበር


ሐካማዝ ኮስሞቲክስና ፕላስቲክ ማምረቻ ኃላ.የተ.የግ ማህበር
የትራንዚተር አገልግሎት የጨረታ ማስታወቂያ

ሐካማዝ ኮስሞቲክስ እና ፕላስቲክ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከውጭ ሀገር የሚያስመጣቸውን የፕላስቲክ ጥሬ ዕቃዎች (PVC/HDPE)፣ የኮስሞቲክስ ግብዓት ጥሬ-ዕቃዎች፣ ማሽነሪዎች እና መለዋወጫዎችን በጅቡቲ ወደብ በኩል (ወደ ሞጆ ወይም ቃሊቲ ደረቅ ወደብ) እንዲሁም በአየር መንገድ (በቦሌ ካርጎ) ፈጣንና ቀልጣፋ የጉምሩክ አስተላላፊነትና የማጓጓዝ አገልግሎት (Customs Clearance and Freight Forwarding/Transit Service) የሚሰጡ ብቁ ተወዳዳሪ ድርጅቶችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

ተወዳዳሪዎች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መሠረታዊ መስፈርቶች:-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የጉምሩክ አስተላላፊነት (Transit) የሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታክስ ክሊራንስ (Tax Clearance) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው፡፡
  4. በማምረቻ ዘርፍ (Manufacturing Sector) ካሉ ፋብሪካዎች ጋር በተመሳሳይ ምርቶች ላይ የላቀ የሥራ ልምድ ያላቸው እና የፋብሪካ የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. የወደብ እና የትራንስፖርት ወጪዎችን በራሳቸው አቅም ከፍለው ዕቃውን በፍጥነት የማስለቀቅ የፋይናንስ አቅም (Credit Limit) ያላቸው፡፡
  6. የጉምሩክ አሠራርን ተከትለው ኮንቴነሮችን በፍጥነት ለማስለቀቅ በቂ እና ብቁ የሆነ የሰው ኃይል ያለው፣
  7. በሃገሪቱ የሚወጡ ህጎች፣መመሪያዎች እና አዋጆች ጠንቅቀው የሚያውቁ፣
  8. ኮንቴነሮች ካለአግባብ ከጉምሩክ ጊቢ እንዳይቆዩ ኃላፊነት ወስዶ በተወሰነ ጊዜ ለማስወጣት ተጠያቂነት መውሰድ የሚችል፣
  9. ድርጅታችንን ወክሎ ከጉምሩክ የሚመጣብንን ጥያቄ መመለስ እና ቀርቦ ማስረዳት የሚችል፣

የማመልከቻ እና የጨረታ አቀራረብ ሁኔታ:-

  • ተጫራቾች የቴክኒክ እና የፋይናንስ (የዋጋ) ማቅረቢያ ሰነዶቻቸውን ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ (Sealed Envelope) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ባለት የሥራ ቀናት ውስጥ ማመልከቻቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በአካል በመምጣት ከዚህ በታች በተጠቀሰው የድርጅቱ ዋና ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል:-

የድርጅቱ አድራሻ:
ሐካማዝ ኮስሞቲክስ እና ፕላስቲክ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ኃይሌ ጋርመንት ላፍቶ ኢንደስትሪ መንደር፣ ከሮሃ ፓክ አጠገብ
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ለተጨማሪ መረጃ ስልክ +251955332977/913567246

  • ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ሐካማዝ ኮስሞቲክስና ፕላስቲክ ማምረቻ ኃላ.የተ.የግ ማህበር

✨ messages.ai_summary
Hakamaz Cosmetics and Plastic Manufacturing seeks qualified firms for customs clearance and freight forwarding of imported plastic raw materials (PVC/HDPE), cosmetics inputs, machinery and spare parts via Djibouti port to Mojo or Kaliti dry port, and by air via Bole cargo. Bidders need a valid transit license, tax clearance, TIN and VAT registration, and manufacturing-sector experience.
Not stated in the notice: opening date, bid security, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender