ለ3B+G+11 ቅይጥ ሕንፃና B+G+7 ሰንበት ት/ቤት ሕንፃ ግንባታ የቁጥጥርና የውል አስተዳደር የማማከር አገልግሎት - ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል
ግልፅ ጨረታ
በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ለ3B+G+11 ቅይጥ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ እና ለB+G+7 ሰንበት ት/ቤት ሕንፃ ፕሮጀክቶች መዋቅራዊ ፍሬም ግንባታ የገንዘብ ክለሳ ፣ የግንባታ ቁጥጥር እና የውል አስተዳደር የማማከር አገልግሎት የወጣ ግልፅ ጨረታ
(የማማከር ሥራ - አማካሪ መምረጥ)
ሀገር:- ኢትዮጵያ
የፕሮጀክቱ ስም:- 3B+G+11 ቅይጥ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ እና B+G+7 ሰንበት ት/ቤት ሕንፃ ግንባታ
መስፈርቶች:-
- የደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን የ3B+G+11 ቅይጥ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ እና የB+G+7 ሰንበት ት/ቤት ሕንፃ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ደረጃ-1 አማካሪ ድርጅት አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ ጋዜጣ ላይ ከወጣ ጀምሮ ለተከታታይ 13 የቀን መቁጠሪያ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታው ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን በ13ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሲሆን በዛው ዕለት 4:30 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የግንባታ ሳይቱን እንዲጎበኙ እና ቅድመ ጨረታ ውይይት እንዲያደርጉ ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ/ም ካቴድራሉ ከጠዋቱ 4:00 ጨረታውን ከገዙ ተጫራቾች ጋር ስብሰባ የሚያካሂድ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 መሣለሚያ የሚገኘው ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ቤተክርስቲያን ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከጠዋቱ 2:00 - 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ 7:00 - 11:00 ሰዓት) የማይመለስ ብር 2,000 (ሁለት ሺ ብር) በመክፈል በአካል ቀርቦ መውሰድ ይቻላል፡፡ ወይም በቴሌግራም @DGKamanuel28 (0921876472) በተጨማሪም በኢሜል amchatederallimat@gmail.com የማይመለስ ብር 2,000 (ሁለት ሺ ብር) በካቴድራሉ ልማት ስም በተከፈተው የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000215809238 በማስገባት የተከፈለበትን ስሊፕ በቴሌግራም በማያያዝ በሶፍት ኮፒ ሰነዶቹን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል:-
- የ 2018 ዓ.ም በተቋቋመው ሀገር ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ወይም የንግድ ድርጅት የምዝገባ ሰርተፍኬት
- ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ለ 2018 ዓ.ም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት
- ተጫራቾች የTIN &VAT ተመዝጋቢ ሰርተፍኬት ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ የግብር ክሊራንስ ሰርተፍኬት ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የመንግስት ግዥ እና ንብረት ባለሥልጣን ዝርዝር የምዝገባ ሰርተፍኬት
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ኦርጅናል ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በተለየ ኤንቨሎፕ በባንክ በተረጋገጠ በካቴድራሉ ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከላይ በተጠቀሱት ተመሳሳይ ፕሮጀክት ሥራዎች ላይ ልምድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
አድራሻ:-
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 መሣለሚያ አካባቢ ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን፣ የካቴድራሉ አስተዳደር ሕንፃ ግራውንድ ወለል :
- ስልክ:- 011-2-76-37-09 / 0927-28-42-92/ 0921-87-64-72
- የፖስታ ሳጥን 14206፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ካቴድራሉ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን
✨ messages.ai_summary
Debre Gelila St. Amanuiel Cathedral seeks a Grade-1 consultant for construction supervision, contract administration, and financial review of a 3B+G+11 mixed-use building and a B+G+7 Sunday school building. Bidders must hold a valid 2018 business license, renewed MoC competency certificate, TIN/VAT registration, tax clearance, and relevant experience.
