Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የቃሊቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address , Phone: +251-0114-62-6451/+251-0114-62-6324
  • Website
  • Deadline09 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 300.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityበሎት ከብር 2,000 እስከ ብር 80,000 (CPO)
  • opening dateበእለቱ 4:30
  • Categories Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather , Laboratory Equipment And Chemicals

የደንብ ልብስ፣ የፅዳትና የጽህፈት ዕቃዎች፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ ጥገና፣ ህትመት እና የላቦራቶሪ ዕቃዎች ግዥ (ግ/ጨ 001/2019) - የቃሊቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የቃሊቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ቃ/ሁ/ደ/ት/ቤት ግ/ጨ 001/2019

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቃሊቲ 2ኛ ደ/ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት:-

  • 1.የደንብ ልብሶች 2.አላቂ የፅዳት ዕቃዎች 3.የቢሮ የፅህፈት መሳሪያዎች 4.ቋሚ ዕቃዎች 5.የጥገና የቧንቧ እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች 6.የህትመት ስራዎች 7.የተለያዩ የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች፣ መድሀኒቶች እና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የተሰማሩበት ንግድ ፈቃድ 1(አንድ) ዓመት የሞላው ከሆነ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. በወጣው ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2:30 እስከ 6:30 እና ከሰዓት ከ7:30 እስከ 11:30 ቢሮ ቁጥር 8 የግዢና ንብረት አስተዳደር ክፍል በአካል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. መ/ቤቱ ለሚገዛቸው ዕቃዎች ናሙና(ሳምፕል) ያቀረበ ሲሆን ናሙና የሚጠየቅባቸውን ዕቃዎች ተጫራቾች ናሙና(ሳምፕል) ጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ቢሮ ቁጥር 8 ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት /ለሚያቀርቡት/ የላቦራቶሪ መገልገያ፣ ጀነሬተር፣ላፕቶፕ እና ሌሎች መሳሪያዎች የሚገልጽ ማንዋል ወይም ዝርዝር መረጃ ከጨረታው ሠነዱ ጋር ተያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን እና ደጋፊ ማስረጃዎቻቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማርኛ መሆን ይኖርበታል፡፡
  9. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ የጨረታ ዋስትና በሎት፡- 6211-54,875.00 ብር፤ 6212-25,113.00 ብር፤ 6213-6,000.00 ብር፤ 6214-3,900.00 ብር፤ 6215-22,159 ብር፤ 6218-29,060.00 ብር፤ 6219-9,242.00 ብር፤ 6223-2,000.00 ብር፤ 6313-80,000.00 ብር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ለሁለት ወር ጸንቶ ይቆያል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በሚመለከት አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  12. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ በመለየትና በፖስታው ላይ በመግለጽ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ቃሊቲ 2ኛ ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ታሽጎ በእለቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
  13. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ:- አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አለፍ ብሎ ቸራሊያ ሳይደርስ በቲተማ በኩል 150 ሜትር ያህል ገባ ብሎ የሚገኘው የቃሊቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251-0114-62-6451/+251-0114-62-6324/+251-0114-39-6550/251-439-4857/ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የቃሊቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Kaliti Secondary School seeks suppliers for uniforms, cleaning and office supplies, furniture, plumbing/electrical maintenance items, printing, and laboratory reagents, medicines and medical equipment. Bidders need a valid/renewed business license, TIN, VAT registration, supplier registration, Amharic documents, and samples where requested.
Save Tender

በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሎት-1 -ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት-2፡ - የፅዳት ዕቃዎች ፣ሎት-3 የደንብ ልብስ፣ሎት-4 የተሽከር...

READ MORE
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት ለማሟያ የሚሆን በአንደኛ ዙር ያልተከናወኑ የሁለተኛ ዙር ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ጥቅል ደ...

READ MORE