Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት
  • Address አዲዮ ወረዳ፣ከፋ ዞን ፣ደቡብ ፣ ኢትዮጲያ, Phone: 0993716652
  • Website
  • Deadline16 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400(አራት መቶ ብር)
  • Bid Securityለሚወዳደሩበት ዕቃ ከጠቅላላ ዋጋ 3% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ
  • opening dateበዕለቱ 4:30 ሰዓት ላይ ቢሮ ቁጥር 02 ይከፈታል
  • Categories Furniture , Stationery Materials , Electronics Materials

የተቋሙ ስም በደቡ/ምዕ ኢትዮጵያ ህ/ ክ/ መ/ በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት 2019 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች የሚውል _ሎት1. አላቂ የጽሕፈት መሳሪያዎችን ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ ሎት 3 የሕንጻ መሳሪያዎችን ሎት 4. የተለያዩ ጀኔሬተሮች ሎት 5. ፈርኒቸሮች እንዲሁም ሎት 6. ደንብ ልብሶች እንዲሁም ሎት 7. የውሃ ግንባታ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የተቋሙ ስም በደቡ/ምዕ ኢትዮጵያ ህ/ ክ/ መ/ በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት 2019 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች የሚውል _ሎት1. አላቂ የጽሕፈት መሳሪያዎችን

  • ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤
  • ሎት 3 የሕንጻ መሳሪያዎችን
  • ሎት 4. የተለያዩ ጀኔሬተሮች
  • ሎት 5. ፈርኒቸሮች እንዲሁም
  • ሎት 6. ደንብ ልብሶች እንዲሁም
  • ሎት 7. የውሃ ግንባታ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

በዚህ መሠረት፡-በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባቸዋል::

  1. በዘመኑ ተጫራቾች ሥራን ለማከናወን የሚያስችል የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለውና በሀገርቱና በክልሉ የግብር አዋጅ በተደነገገው መሠረት የግብርና የታክስ ግደታውን የተወጣ ፎቶ ኮፒዎችን አያይዞ ማቅረብ የሚችል/የምትችል/
  2. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል/የምትችል/
  3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 400 ብር/አራት መቶ ብር/በመክፈል ከግዥና ንብረት አስ/ር ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 በአካል ቀርበው መግዛት ይኖርባቸዋል::
  4. ተጫራቾች በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ዕቃ ከጠቅላላ ዋጋ 3% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በአዲዮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም አዘጋጅተው ማቅረብ ይኖርበታል::
  5. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ዋውንና ኮፒውን ስልጣን ባለው አካል ተፈርሞ ማህተም ተደርገው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በቢ.ሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  6. ጨረታውን በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ታሽገው በዕለቱ 4:30 ሰዓት ላይ ቢሮ ቁጥር 02 ይከፈታል፤ሆኖም ግን 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን የተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም::
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ማካተቱን እና አለማካተቱን መግለጽ ይኖርባቸዋል፤ሆኖም ግን ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ቫትን ስለማካተቱና አለማካተቱ በግልጽ ያመለከቱ ከሆነ የቀረበው ዋጋ ቫትን እንዳካተተ ተደርገው ይወሰዳል::
  8. ተጫራቾች የፋይንሻል እና የቴክኒክ መገምገሚያ መስፈርቶችን በመሙላትና በተለያዩ አራት ፖስታዎች በማሸግ በፖስታው ላይ የፋይንሻል ኦርጅናል እንዲሁም ኮፒ የቴክኒክ ኦርጅናል እንዲሁም ኮፒ መሆኑን በመግለጽ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  9. አሸናፊ ድርጅቶች እንደአስፈላጊነቱ ውል ከመግባታቸው በፊት መ/ቤቱ የጠየቀውን የዕቃ ናሙና ማቅረብ መቻል ይኖርባቸዋል::
  10. ተጫራቾች የሚሞሉት የዕቃ ዋጋ ላይ መለኪያና ጥራቱን ጠብቀው መሙላትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  11. በመንግስት ግዥ ላይ እንዳይሳተፍ እገዳ የተጣለበት ከሆነ የዕገዳ ጊዜውን ያጠናቀቀ መሆኑን የሚገልጽ መረጃ አያይዘው ማቅረብ መቻል ይኖርበታል::
  12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከወጣው ጨረታ ውስጥ ከብር 200,000 ብር/በፊደል/ ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያም በላይ ባለው ግዥ የሚሳተፉ ማንኛውም የሀገር ውስጥ ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት::
  13. አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ተገልፆ በሚሰጠው የዕቃ ግዥ ትዕዛዝ መሠረት ዕቃዎቹን በራሱ ወጪ እስከ መ/ቤቱ የዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት የማቅረብ ግዴታ አለበት::
  14. ውል የሚፈጽም ማንኛውም ሰው ውል ለመፈጸም የሚያስችል የህግ ችሎታ ያለው መሆን ይኖርበታል::
  15. በዕዳ ያልተያዘ ያልከሰረ ወይም የስራ እንቅስቃሴውን ያላቋረጠ እንዲሁም የንግድ ሥራ እንቅስቃሴው ያልታገደ ወይም በእነዚህ ምክንያቶች ተከሶ በክርክር ላይ ያልሆነ::
  16. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ በጽሑፍ ከተገለጸለት በኋላ ባሉት ሰባት ቀናት ውስጥ የውል ሰነድ በመውሰድ መፈራረም አለበት፤ውሉን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ካልገባ የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል::
  17. የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  18. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ማብራሪያ ከፈለጉ በግዥና ንብረት አስተዳደር ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0917003400/0900945892/0988915803 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ::

ማሳሰቢያ፡-መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

በካፋ ዞን የአዲዮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender by Adio Woreda Finance Office (Kafa Zone, SW Ethiopia) for sector offices: office stationery, electronics, building tools, generators, furniture, uniforms, and water construction materials, in 7 lots. Bidders need a valid trade license, tax clearance, VAT registration, and TIN.
Save Tender