Tender Detail

Tender Details

  • Company Tikur Abay Transport PLC (ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማ/)
  • Address አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጋዜቦ አደባባይ ስተረሊንግ ህንጻ 3ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-552-7748
  • Websitehttps://tikurabaytl.com/
  • Deadline09 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 500 (የማይመለስ)
  • Bid Securityየጠቅላላ ዋጋ 2% (CPO)
  • opening dateበዚሁ ቀን 4:30
  • Categories Disposal Sale , Vehicle Spare Parts

ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በተለያየ ምክንያት በኩባንያው ስቶር ውስጥ እና ከስቶር ውጪ የተከማቸ የተለያየ ሞዴል መኪኖች መለዋወጫ፣ ዘይት እና የመሳሰሉትን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Tikur Abay Transport PLC (ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማ/)


የተሽከርካሪ መለዋወጫ ጨረታ ማስታወቂያ

ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በተለያየ ምክንያት በኩባንያው ስቶር ውስጥ እና ከስቶር ውጪ የተከማቸ የተለያየ ሞዴል መኪኖች መለዋወጫ፣ ዘይት እና የመሳሰሉትን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ከዚህ በታች በተገለፀው የጨረታ መመሪያ መሠረት እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የተለያየ ሞዴል መኪኖች መለዋወጫ፣ ዘይት እና የመሳሰሉትን በሚገኙበት ኮምቦልቻ ጋራዥ እና አዳማ ቅ/ፍ ስቶር ዘወትር በሥራ ሰዓት በመሄድ የገዙትን ጨረታ ሰነድ በማሳየት ስፔር ፓርቱን በአካል ማየት ይቻላል፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በጨረታ ሠነዱ ላይ የሞሉትን ዋጋ የጠቅላላ ድምሩ 2% ጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማስገባት ውድድሩን መሳተፍ ይቻላል፡፡
  3. ሌላው በሚያቀርበው የጨረታ ዋጋ ላይ በመንተራስ በፐርሰንት አሳንሶ ወይም አስበልጦ የጨረታ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ካወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናቶች ዘወትር በሥራ ሰዓት ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ የማይመለስ በመክፈል ኮምቦልቻ ዋና መ/ቤት ገንዘብ ቤት እና አዳማ ቅ/ፍ ጽ/ቤት በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው የጨረታ ሳጥኑ ከመታሸጉ በፊት አዳማ ቅ/ፍ ጽ/ቤት፣ አዲስ አበባ ማስ/ጽ/ቤት እና ኮምቦልቻ ዋና መ/ቤት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታው መዝጊያ ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:30 በሥራ ሰአት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮምቦልቻ ዋናው መ/ቤት፣ አዲስ አበባ ማስ/ጽ/ቤት እና አዳማ ቅ/ፍ ይከፈታል ነገር ግን 16ተኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተቀመጠው ሰዓት ላይ የሚከፈት እና የሚዘጋ ይሆናል፡፡
  7. የጨረታው አሸናፊዎች ጨረታውን ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ በ8 /ስምንት/ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ሙሉ በሙሉ መክፈል ይጠበቅባቸዋል፤ በስምንት ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ ማድረግ ካልቻሉ አሸናፊነታቸው ተሰርዞ ያስያዙት ገንዘብ አይመለስላቸውም።
  8. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን በ10 /አስር/ የሥራ ቀናት ውስጥ መውሰድ ይኖርባቸዋል።
  9. በጨረታው ለተሸነፉት ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል።
  10. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ለተጨማሪ ማብራሪያ የስልክ ቁጥር ኮምቦልቻ 033 551 4219 አዳማ 022 112 6241 አዲስ አበባ 011 557 5115

ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርት እና ሎ/ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር

✨ messages.ai_summary
Tikur Abay Transport PLC is selling assorted vehicle spare parts and oil, stored both inside and outside its store, via competitive bid. Bidders may inspect the items in person at the Kombelcha garage and Adama branch store during working hours. The company reserves the right to cancel the tender in whole or in part.
Save Tender