Tender Detail

Tender Details

  • Company የአምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0112609010
  • Website
  • Deadline13 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 200 (የማይመለስ)
  • Bid Securityየጠቅላላ ዋጋ 1% (CPO)
  • opening date04/03/2019 ዓ.ም 4:30 ሰዓት
  • Categories Sport Materials And Sportswear

የአምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ በማዕከሉ ለሚያሠለጥናቸው ሠልጣኞችና አሠልጣኞች የተለያዩ የስፖርት ትጥቆችና የስልጠና ቁሳቁሶች የክልሉ መንግሥት ባወጣው የግዢ አዋጅ ቁጥር 157/2002 በመከተል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የአምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ


2ኛ የጨረታ ማስታወቂያ

የአምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ በማዕከሉ ለሚያሠለጥናቸው ሠልጣኞችና አሠልጣኞች የተለያዩ የስፖርት ትጥቆችና የስልጠና ቁሳቁሶች የክልሉ መንግሥት ባወጣው የግዢ አዋጅ ቁጥር 157/2002 በመከተል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ዝርዝር ሁኔታዎች

ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ : ስለ እስፓርት ትጥቆች የሚገልጽ ዝርዝር ሰነድ ዶክመንት/ የማይመለስ ሁለት መቶ (200) የኢትዮጵያ ብር በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት በአምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ውስጥ በጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

የተጫራቾች ግዴታ

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ከሆኑ፣ተመዝጋቢ ስለ መሆናቸው የሚገልጽ ማሥረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ የሚችሉ።
  4. የታደሰ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸውና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  5. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ የኢትዮጵያ ብር 1% በCPO በ ሰንቄ ባንክ በማስገባት የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል:
  6. በአገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በአቅራቢነት የተመዘገቡና ሰርተፍኬት ያላቸው እና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ።
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ኮፒና ዋናውን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት 13/02/2019 እስከ 03/03/2019 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት በአምቦ እግር ኳስ ማሠልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ ቢሮ ቁጥር 6 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይችላሉ ። ከላይ በተገለጸው መሥሪያ ቤት አዳራሽ ውስጥ በ16 ኛው ቀን በ04/03/2019 ከቀኑ 4 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት (ባይገኙበትም) በ 4:30 ሰዓት ይከፈታል።
  8. አሸናፊው ድርጅት ማናቸውንም አስፈላጊ ወጭዎች ችሎ ያሸነፈባቸውን የስፖርት ትጥቆችና ቁሳቁሶች በሰዓቱ በማዕከሉ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ።
  9. ማዕከሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0112609010 ፣ 0913286868 ወይም 112602341 አምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የአምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል

✨ messages.ai_summary
Ambo Goal FIFA Football Training Center seeks sports kits and training materials for its trainees and coaches via open tender. Bidders must have a valid business license, tax payment proof, TIN, VAT registration if applicable, and supplier registration certificate.
Save Tender