Tender Detail

Tender Details

  • Company የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ /ኢ/ል/ጽ/ቤት
  • Address ሚዛን አማን ከተማ : ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline09 Nov 2026, 9:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceበነጻ
  • Bid Securityብር 30,000 (CPO፣ የባንክ ዋስትና ወይም LC)
  • opening dateበዚያው ቀን 4:00 ሰዓት
  • Categories Food Items And Drinks , Agricultural Products

የሚዛን አማን ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በሚዛን አማን ከተማ ደረጃ አንገብጋቢ ለሆኑ ጉዳቶች የተፈጥሮ አደጋን በራስ አቅም መከላከል ታሳቢ በማድረግ የእህል ዓይነቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ /ኢ/ል/ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የሚዛን አማን ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በሚዛን አማን ከተማ ደረጃ አንገብጋቢ ለሆኑ ጉዳቶች የተፈጥሮ አደጋን በራስ አቅም መከላከል ታሳቢ በማድረግ የእህል ዓይነቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላል።

  1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው
  3. በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ኦንላይን የተመዘገቡና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
  5. ግብር ስለመክፈላቸው ከገቢዎች መ/ቤት ክሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  6. የጨረታ ሰነድ ከግዥ ኬዝ ቲም የሥራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን /በነጻ/ በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።
  7. የጨረታ ሰነዱ ሞልተው ሲመልሱ ህጋዊነት ሰነድ እና ፋይናንሻል የተሞላበትን ሰነድ 1 ኦርጅናልና 1 ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. የጨረታ ማስከበሪያ 30,000/ሰላሳ ሺ ብር/ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ቼክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ለሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በማለት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3:30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ4:00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
  10. ሰነዱን ሞልተው ወደ ጨረታ ሳጥን ለማስገባት ሲመጡ ተመዝግበውና ፈርመው ማስገባት አለባቸው
  11. በጨረታ ማስታወቂያ ላይ የቃላት ወይም የትርጉም ስህተት ቢኖር በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጠው የበለጠ ተቀባይነት ይኖረዋል።
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Mizan Aman city finance office seeks bidders to supply food grains for disaster preparedness. Bidders must have a renewed business license, VAT and TIN registration, online supplier registration certificate, and tax clearance. Bid documents are free from the procurement office.
Save Tender