Tender Detail

Tender Details

  • Company South Ethiopia Regional State Transport and Road Development Bureau (የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ)
  • Address ዲላ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0461316004
  • Website
  • Deadline04 Nov 2026, 5:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 1000 (የማይመለስ)
  • Bid Securityሎት 1፣2 እና 3 ለእያንዳንዱ ብር 50,000፤ ሎት 4 እና 5 ለእያንዳንዱ ብር 20,000 (CPO ወይም ባንክ ጋራንቲ)
  • opening dateበ16ኛው ቀን 4:30
  • Categories Software & Applications Development , Software Provision, Development And Web Design

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት አስተዳደር ቢሮ በክልሉ ሥር በሚገኙ መናኸሪያዎች አገልግሎት የሚሰጡ ብቃት ያላቸውን የኢቲኬቲንግ ትግበራ ሶፍትዌር አቅራቢ ድርጅትን፣ ማህበርን ወይም ግለሰብን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውለታ ለማሰራት ይፈልጋል።

South Ethiopia Regional State Transport and Road Development Bureau (የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ)


የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 008/2019

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት አስተዳደር ቢሮ በክልሉ ሥር በሚገኙ መናኸሪያዎች አገልግሎት የሚሰጡ ብቃት ያላቸውን የኢቲኬቲንግ ትግበራ ሶፍትዌር አቅራቢ ድርጅትን፣ ማህበርን ወይም ግለሰብን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውለታ ለማሰራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት:-

ሎት ቁጥር የሚገኝበት ዞን የመናኻሪያ ብዛት አገልግሎት የሚሰጠው መናኻሪያ
1 ወላይታ ዞን 6 ቦዲቲ፣ አረካ፣ ሁምቦ፣ ጉኑኖ፣ ገሱባ እና በሌ ሆሞሳ
2 ጋሞ ዞን 5 ሰላምበር፣ ጨንቻ፣ ዋጁፎ፣ ገረሴ እና ብርብር
3 ጌዴኦ ዞን 4 ይ/ጨፌ፣ ገደብ፣ ጨርሶ እና ወናጎ
4 አሪ ዞን 1 ጂንካ
5 ኮንሶ 1 ካራት
  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ አመታዊ የስራ ግብር የከፈሉበትን፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ አያይዘው ጨረታ ሰነድ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የሥራውን ዝርዝር እስፔስፊኬሽንና የጨረታ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 17 ድረስ መጥተው የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15/አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን 11:30 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን 4:30 ላይ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት /Lot/ 1,2 እና 3 ለእያንዳንዱ 50,000 (ሀምሳ ሺህ) ብር እና ለሎት /Lot/ 4 እና 5 ለእያንዳንዱ 20,000 /ሃያ ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ወይም ባንክ ጋራንቲ በቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ ውስጥ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ፣ ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸውን ለየ ብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እና ጠቅላላውን በአንድ በአናት ፖስታ ታሽጎ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 11:30 ድርስ ቢሮው ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  6. ተጫራቾች ሶፍትዌር ልማት ማረጋገጫ እና የሶፍትዌር ደህንነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ የተቀመጡ ሌሎች ዝርዝር መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው።
  7. ተጨማሪ መረጃ ከሰነዱ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እያሳወቅን የደቡብ /ኢ/ክ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት አስተዳደር ቢሮ እንደገና ተሻሽሎ የወጣው የግዢ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 70/2017 እና መመሪያው ላይ የተደረገውን ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ሰርኩላር ተፈጻሚ ይደረጋል።

ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ ማብራሪያ:- በስልክ ቁጥር 0916029511/0913725758 መደወል ይችላሉ አድራሻ:- ዲላ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት አስተዳደር ቢሮ

✨ messages.ai_summary
The South Ethiopia Regional Transport and Road Development Bureau seeks a qualified e-ticketing software provider (firm, association, or individual) to implement e-ticketing at terminals across five zones. Bidders need a renewed business license, VAT registration, tax compliance, supplier certificate, and software development and security certificates.
Save Tender