የሲንግል ሀመር ክሬሸር መለዋወጫ (Single Hammer Crusher Spare Parts) ግዥ (ሙሲፋ/07/2019) - ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)
የሀገር ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ሙሲፋ/07/2019
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት ሲንግል ሀመር ክሬሸር ስፔር ፓርት (Single Hammer Crusher Spare Parts) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው (የ2018/2019 ዓ.ም)፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 (አምስት መቶ ሰባ አምስት) ከከፈሉ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ገርጂ አካባቢ የቀድሞው ኢምፔሪያል ሆቴል መደረሻ ወለል ከሚገኘው የፋብሪካው ግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የአጠቃላይ ዋጋ 2% በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (C.P.O) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቱ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡ ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
