ጨረታ ቀነ-ገደብ ማራዘሚያ – የኢንፕልመንት መሳሪያዎች መለዋወጫና ግብዓቶች እና የመካኒካል ወርክሾፕ ማሽኖች ግዥ (NCB AAMMI/NCB/003/2026 እና NCB AAMMI/NCB/002/2019)
በኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ
ለሚመለከተው ሁሉ
በጨረታ ሰነድ ቁጥር ቁ-NCB AAMMI/NCB/003/2026 በቀን 18/01/19 ዓ.ም በወጣ በኢንዱስትሪው ለሚመረቱ የኢንፕልመንት (ማረሻ፣ መከስከሻ፣ጋሪ) መሳሪያዎች ምርት አገልግሎት የሚውሉ የመለዋወጫና የግብዓት ግዥ እና በጨረታ ሰነድ ቁጥር ቁ-NCB AAMMI/NCB/002/2019 በቀን 23/01/19 ዓ.ም በወጡ እና ለተለያዩ ኦፕሬሽናል ስራዎች አጋዥ የሆኑ የመካኒካል ወርክ ሾፕ ማሽኖች ግዥ የጨረታ ማስገቢያ ቀነ-ገደብ ስለ ማራዘም ይመለከታል፡፡
አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በጨረታ ሰነድ ቁጥር ቁ-NCB AAMMI/NCB/003/2026 በቀን 18/01/19 ዓ.ም በወጣ በኢንዱስትሪው ለሚመረቱ የኢንፕልመንት (ማረሻ፣መከስከሻ፣ጋሪ) መሳሪያዎች ምርት አገልግሎት የሚውሉ የመለዋወጫና የግብዓት ግዥ እና በጨረታ ሰነድ ቁጥር ቁ-NCB AAMMI/NCB/002/2019 በቀን 23/01/19 ዓ.ም በወጣ ለተለያዩ ኦፕሬሽናል ስራዎች አጋዥ የሆኑ የመካኒካል ወርክ ሾፕ ማሽኖች ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ አየር ላይ ያወጣን ሲሆን በዚህም በጨረታው መመሪያ መሰረት የሁለቱም ግዥዎች የጨረታ ማስገቢያ ቀን ገደብ ጥቅምት 9/2019 ዓ.ም ቢሆንም ነገር ግን በተጫራቾች በኩል የጨረታ ማስገቢያ ቀነ-ገደቡ እንዲራዘም የቀረበውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ በተወሰነ ደረጃ የጨረታዎቹ የቴክኒካል ስፔስፍኬሽን ዝግጅት በወቅቱ ያልተጠናቀቀ በመሆኑ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ዘግይቶ የጀመረ በመሆኑ በጨረታዎቹ የቀረቡ ቴክኒካል ፍላጎቶችና መመዘኛዎች ሰፊ በመሆናቸው ለተወዳዳሪዎች በቂ የዝግጅት ጊዜ እንዲኖር ያስችል እና ከኢንዱስትሪው ጥቅም አንጻር በቂ ተወዳዳሪዎች ለማሳተፍ ሰፊ የገበያ ዕድሎችን ለመመልከት እንዲያስችለን የሰነድ ማስገቢያ ቀን ገደቡ ማራዘም የታመነበት በመሆኑ የጨረታ ማስገቢያ ቀነ-ገደቡ እስከ ጥቅምት 30/2/2019 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
