የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ የሚያስፈልጉ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የጨረታ ሎቶች ለሁለተኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ የሚያስፈልጉ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የጨረታ ሎቶች ለሁለተኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1. የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት
ሎት 2. የዲኮር ግብዓቶች እና ሌሎች አገልግሎቶች በኪራይ
ሎት 3. የፕሮቶኮል ልብስ
ሎት 4. የተፈጥሮ ውሃ
ሎት 5. የባህል ልብስ
ሎት 6. የደንብ ልብስ
በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 400 በመክፈል ሰነዱን ከግዢ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 105 1ኛ ፎቅ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት 1000011113625 አዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት ከአጠቃላይ ዋጋ CPO 2% በማስያዝ የባንክ እስሊፑን ይዘው መምጣት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የውል ማስከበሪያ 10% (አሥር በመቶ) CPO በማስያዝ ከም/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ በየሎቱ ዋናውና ኮፒውን ለየብቻው ተፈርሞበት በየገፁ ማህተም በማድረግ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ መሆን አለበት ይህ ሳይሆን ሲቀር መ/ቤቱ ቫት እንደተካተተ አድርጎ ይወስዳል፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ፡፡
- በሎት 1 ሜኑ ሎት 3፣5፣ ሎት 6 የምትወዳደሩባቸውን ናሙና መቅረብ አለበት፡፡
- ተወዳዳሪዎች ለተመሳሳይ አገልግሎት ተመሳሳይ ዋጋ ካቀረቡ በዕጣ የሚለይ ይሆናል፡፡
- ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- በጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3:30 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ በ4:00 ሰዓት ተወዳዳሪዎች በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ውል ከተዋዋለ በኋላ ዋጋ መጨመርና መቀነስ የማይቻል መሆኑ፣
- መ/ቤቱ ከተገኘው ዋጋ ሳይቀይር እስከ 25% የእቃውን ወይም አገልግሎቱን መቀነስ ወይም መጨመር የሚችል መሆኑን፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ
የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎች፣
- የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የምሥክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ምዝገባ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በሎት 1 የሚወዳደሩ በሥራ ዘርፉ ለመሰማራታቸው የብቃት ማረጋገጫ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ
አድራሻ፡-ከሳንቺስ ልማት ባንክ ጀርባ
ስልክ ቁጥር ፡-091304 35 09 ይደውሉ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Addis Ababa City Council Office seeks second-round open bids for hotel/hospitality services, decor materials and rental services, protocol uniforms, natural water, traditional clothing, and uniforms. Bidders must submit tax payment proof, renewed trade/business licenses, VAT registration, and for Lot 1 a Ministry of Culture and Tourism competency certificate.
