ፀሀይ ኢንሹራንስ አ.ማ ከታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች የሰው ኃይል አቅራቢ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለዋና መ/ቤት እና ለተለያዩ ቅርንጫፍ ቢሮዎቹ ማሰራት ይፈልጋል።
Tsehay Insurance S.C.
ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ.
የሰው ሃይል አገልግሎት ግዥ
ግልፅ ጨረታ
ቁጥር.: ፀኢ/ግንአ/005/2019
ፀሀይ ኢንሹራንስ አ.ማ ከታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች የሰው ኃይል አቅራቢ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለዋና መ/ቤት እና ለተለያዩ ቅርንጫፍ ቢሮዎቹ ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን የጨረታ መመሪያ እና መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ፍላጎት ያላቸው ተወዳዳሪዎች መወዳደር ይችላሉ።
ሎት 1፡-የጥበቃ አገልግሎት
ሎት 2፡-የፅዳት አገልግሎት
- ተወዳዳሪዎች ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሥራና አሰሪን ለማገናኘት የተሰጠ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ።
- የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉበትን የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ተ.እ.ታ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት እና ታክስ ክሊረንስ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
- የጨረታ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቦሌ ድልድይ የቀድሞ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው 3ኛ ፎቅ የኩባንያው የፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ፣ ከጥቅምት 09/2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም ድረስ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ዋጋ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ይሆናል። ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡት ዋጋዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ ሆኖ፣ ማንኛውንም ወጪና የመንግስት ቀረጥ የተከፈለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
- ግልጽ ጨረታው ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ጠዋት 4:15 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መሥሪያ ቤት ቦሌ ድልድይ፣ የቀድሞው ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት
ስልክ፡ +251 111 119 70 /71
