Tender Detail

Tender Details

  • Company የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት (Defence Construction Design Enterprise)
  • Address ካሳንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደም ስኳር ኮርፖሬሽን የነበረበት የኪያ-ሜድ ኮሌጅ ህንጻ ግራውንድ ላይ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 896 06 33
  • Websitehttps://dcde.gov.et/#
  • Deadline02 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Priceብር 500.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 432,000.00 (CPO ወይም የባንክ ዋስትና)
  • opening dateበዚሁ ቀን ከቀኑ 4:30
  • Categories Automotive Materials

የፒክአፕ እና የኤሌክትሪክ ሚኒ-ባስ ተሽከርካሪዎች ግዥ (DCDE 002/2019) - የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት (Defence Construction Design Enterprise)


የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCDE 002/2019

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ ፒክአፕ እና የኤሌክትሪክ ሚኒ-ባስ ተሽከርካሪዎች ግዥ ከተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

  1. ማንኛውም ተጫራች ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ታክስ ክሊራንስ፣የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የውጪ አገር ተጫራቾች በሚሆኑበት ጊዜ በተቋቋሙበት አገር የተሰጣቸውን የኩባንያ ምዝገባ ወረቀት ወይም ፈቃድ፣የአገር ውስጥ አምራች ወይም ገጣጣሚ ወይም የአምራች ህጋዊ ወኪል ማስረጃ(letter of authorization) የግጣጣሚ ህጋዊ ፈቃድ ወዘተ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱ በድርጅታችን ፋይናንስ ዴስክ መውሰድ ይጠበቅባችኋል፡፡
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በTOR በተያያዘው ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡
  4. ጨረታው ከጥቅምት 8 ቀን 2019 እስከ ጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ.ም አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ይካሄዳል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዢ ዴስክ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአከፋፈት ሂደት ባይገኙም የጨረታው የአከፋፈት ሂደት አያግደውም፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ከላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በድርጅቱ የግዥ ዴስክ አራተኛ ፎቅ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ድርጅታችን ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የህዝብ በአል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይተላለፋል፡፡
  8. የጨረታ ማስከበሪያ እንደ ተጫራቹ ምርጫ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ(CPO) ብር 432,000.00(አራት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺ ብር) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡

አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 5570640
አድራሻ ካሳንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደም ስኳር ኮርፖሬሽን የነበረበት የኪያ-ሜድ ኮሌጅ ህንጻ አራተኛ ፎቅ

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Defence Construction Design Enterprise seeks to buy pickup and electric mini-bus vehicles for its own service use via open tender. Bidders must submit VAT registration and TIN certificate, commercial registration, renewed tax clearance, renewed business licence, and, for foreign bidders, company registration/licence from their country; local manufacturers/suppliers need authorization letters.
Save Tender