Tender Detail

Tender Details

  • Company የወጣት ሴቶች ክርስቲያናዊ ማህበር በኢትዮጵያ (YWCA in Ethiopia)
  • Address , Phone: +251 111704742/0968570579
  • Website
  • Deadline23 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date13/02/2019 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ሰዓት
  • Categories Automotive Materials

በነዳጅ የሚሰራ ተሽከርካሪ (Suzuki Alto ወይም ተመጣጣኝ) ግዥ - የወጣት ሴቶች ክርስቲያናዊ ማህበር በኢትዮጵያ (YWCA in Ethiopia)

የወጣት ሴቶች ክርስቲያናዊ ማህበር በኢትዮጵያ (YWCA in Ethiopia)


ግልጽ ጨረታ
የወጣት ሴቶች ክርስቲያናዊ ማህበር በኢትዮጵያ
(YWCA in Ethiopia)

የወጣት ሴቶች ክርስቲያናዊ ማህበር በኢትዮጵያ (YWCA in Ethiopia) አለማቀፋዊ ይዘት ያለው፣ በበጎ ፈቃደኝነት የሚንቀሳቀስ መንግሥታዊ ያልሆነ ማህበር ነው፡፡ ማህበሩ የዘርም ሆነ የሃይማኖት ልዩነት ሳያደርግ መልካም ስብዕና ያላቸውና በበጎ ሥነ-ምግባር የታነፁ ዜጎችን፣ በተለይም ዜጎችን ለማፍራት፣ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ለችግር የተጋለጡ ወጣት ሴቶችን አቅም ለማጎልበት በፌዴራል የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በቁጥር 0237 ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ ሀገር በቀል ድርጅት ነው፡፡

ድርጅቱም በነዳጅ የሚሰራ ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ተሽከርካሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ይህን ጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ከጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በቢሮው በመገኘት በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡

የተሽከርካሪው ቴክኒካዊ መስፈርቶች

  • የመኪና አይነት፡……በነዳጅ የሚሰራ ተሽከርካሪ
  • ተመራጭ ሞዴል፡…Suzuki Alto ወይም ተመጣጣኝ ሌላ ሞዴል
  • የሞዴል ዓመት፡……2022—2025
  • የሞተር አቅም፡……1000 CC እና ከዚያ በላይ
  • የሲሊንደር ብዛት፡…3 ወይም 4 ሲሊንደር
  • የነዳጅ አይነት፡………Petrol
  • ከፍተኛ ፍጥነት፡……140 - 80 KM/H
  • የመቀመጫ ብዛት፡…5 መቀመጫ
  • የበር ብዛት፡…………4 በር

ተጫራቾች ማቅረብ የሚገባቸው ሰነዶች፡-

  1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፡፡
  2. የዘመኑ ግብር ለመክፈሉ ማረጋገጫ ከተገቢው መ/ቤት፡፡
  3. በንግድ ድርጅት የተመዘገበ የቲን ቁጥር ያለው እና ቫት ተመዝጋቢ መሆኑን ማረጋገጫ፡፡
  4. ብቸኛ አስመጪ ከሆነ የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ፡፡
  5. ተሽከርካሪውን ማቅረብ የሚችሉበትን የጊዜ ገደብ መግለጽ፡፡

የጨረታ መክፈቻ

ጨረታው ጥቅምት 13/02/2019 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በYWCA Ethiopia ቢሮ ይከፈታል፡፡

አድራሻ፡-

የወጣት ሴቶች ክርስቲያናዊ ማህበር በኢትዮጵያ (YWCA Ethiopia)
4 ኪሎ፣ አክሱስ ሕንፃ፣ ከብሄረሆት ሳይበራረ አጠገብ፣ 4ኛ ፎቅ
ስልክ፡- +251 111704742/0968570579

የወጣት ሴቶች ክርስቲያናዊ ማህበር በኢትዮጵያ (YWCA in Ethiopia)

✨ messages.ai_summary
YWCA Ethiopia seeks to buy a petrol-powered vehicle (Suzuki Alto or equivalent): model year 2022–2025, engine 1000 CC or more, 3 or 4 cylinders, 5 seats, 4 doors. Bidders must submit a renewed trade license, tax payment proof, TIN/VAT registration, sole-importer evidence if applicable, and a delivery timeline.
Not stated in the notice: bid security, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender