4 የዘይት መጭመቂያ ማሽኖች እና አንድ መፈልፈያ ማሽን የሐራጅ ሽያጭ (ቡራዩ፣ መነሻ ብር 2,800,000) - የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፀፀም ጽ/ቤት
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት አቶ አህመድ አሰፋ ሙዘሚል እና የፍ/ባለዕዳ እነ ኤም ኤስ ጂ አስመጪና ላኪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/22641 በ5/09/2018ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/25332 በ13/11/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቡራዩ ክ/ከተማ ገፈርሳ ወረዳ የቤት ቁጥር የፍ/ባለዕዳ መጋዘን ውስጥ የሚገኙ ሞዴል 2X130 የሆኑ 4 የዘይት መጭመቂያ ማሽኖች እና ሞዴል DGP 120-11 የሆነ አንድ መፈልፈያ/ማብሰያ/ማሽን የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 2,800,000 (ሁለት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሺህ) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 23 ቀን 2019ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
