ተቋማችን ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዓይነት የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን (ፈርኒቸሮች) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ምሥራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ጽ/ቤት
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ምስ/አ/አ/ሪ/ግ/ጨ/002/2019
ተቋማችን ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዓይነት የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን (ፈርኒቸሮች) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
| ሎት | የዕቃው ዓይነት | የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) | የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት | የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
| 1 | የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን (ፈርኒቸሮች) | 114,655.00 | ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት | ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈ.ቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር EEU-EAAR CONNECTION FEE. (1000298392902) በሚለው ገቢ በማድረግ እና የከፈሉበትን የባንክ ስሊፕ ይዞ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- አድራሻ፡- ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን 1ኛ ፎቅ ላይ ሰፕላይ ቼይን ግዥ እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና <ETHIOPIAN ELECTRIC UTILITY> በሚል መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ከላይ እስከ ተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓት እና አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Electric Utility's East Addis Ababa Region office seeks to buy various office furniture through open tender. Eligible bidders must be sector-engaged, have a renewed business license, VAT registration, tax clearance, and a taxpayer ID.
