የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ሠራተኞች የተለያዩ ዓይነት የደንብ ልብሶች የስፌት አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
Ethiopian Electric utility project portfolio Management
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEU/PPM/05/2019(NCB)
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ሠራተኞች የተለያዩ ዓይነት የደንብ ልብሶች የስፌት አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ::
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ፣ በኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ ገጽ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የኢ.ኤ.አ. ፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ከካቴድራል መብራት ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ ከኤንሪኮ ኬክ ቤት 150 ሜትር ርቀት በሚገኘው ዋስትና የንግድ ማዕከል 11ኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የዋስትና ጊዜው ከሚያበቃበት ቀን በኋላ 28 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ያለው የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) በኢ.ኤ.አ. ፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ወይም EEU-PPM ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እና ጨረታ ቁጥር EEU/PPM/05/2019(NCB) የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ በኢ.ኤ.አ. ፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ዋስትና የንግድ ማዕከል ህንጻ ላይ 11ኛ ፎቅ በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል::
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ የጨረታ ሰነዱን በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2:00-6:00 ከሰዓት 7:00-11:00 እና ቅዳሜ ጠዋት ከ 2:00-6:00 መመልከት ይቻላል::
- የፕሮግራም ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0111263153 መደወል ይችላሉ::
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
የፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Electric Utility Project Portfolio Management seeks sewing services to produce various uniforms for its staff. Eligible bidders must be licensed in the field, provide tax payment proof, renewed business license, VAT registration, and proof of registration on the Federal Government Procurement Agency supplier list.
