የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት ለሰራዊቱ አገልግሎት የሚውል የደንብ ልብስ አልባሳት ግዢ ለመፈጸም ጨረታ ለማውጣት ስለምንፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል ፡፡
Dire Dawa Administration Police Commission (የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን)
የጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት ለሰራዊቱ አገልግሎት የሚውል የደንብ ልብስ አልባሳት ግዢ ለመፈጸም ጨረታ ለማውጣት ስለምንፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል ፡፡
- የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ለ15 ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት የሥራ ሒደት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ ፣ተጨማሪ እሴት ታክስ ፤ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆንና የጨረታው ውጤት እንደታወቀ የሚመለስ የሚጫረቱበት፤ ብር 400,000.00/አራት መቶ ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO/ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ተመራጭነት አለው፡፡
- የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ለየብቻ በፖስታ በማሸግ በአንድ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
የጨረታ ሰነድ ጥቅምት 3 /2019 ዓ/ም እስከጥቅምት 17 /2019 ዓ.ም. ከ11፡00 ሰዓት በድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን በፋይናንስና ግዢ አስተደረር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 18 /2019.ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሣጥኑ ታሽጎ 3፡30 ሠዓት ይከፈታል፡፡
ፖሊስ ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0251-11-74-55/0251-11-37-43 በመደወል መረጃ ፖ.ሣ.ቁጥር 1453 ማግኘት ይችላሉ፡፡
የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን
✨ messages.ai_summary
Dire Dawa Police Commission invites eligible bidders to supply uniform clothing for its force. Bidders must submit business registration, valid trade license, tax payment proof, VAT and supplier certificates. Partial or full cancellation of the tender is reserved.
