Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline30 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ግምቱ 1/4 (ብር 45,000) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ CPO
  • opening dateምዝገባው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ
  • Categories Machinery , Disposal Sale

የሽመና ማሽን የሐራጅ ሽያጭ (መነሻ ብር 180,000) - የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፀፀም ጽ/ቤት

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት ወለተማሪያም ደምሰው እና በፍ/ባለዕዳ አነ አብይ ማሽን ማምረቻ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 175020 በ06/9/2018 ዓ/ም እና መ/ቁ 177686 በ30/11/018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 05 የቤት ቁጥር አዲስ ውስጥ የሚገኝ የሐገር ውስጥ የሽመና ማሽን(መደወሪያና ማዳሪያ ያለው ጭምር የሐራጅ ሽያጭ መነሻ 180,000 (አንድ መቶ ሰማንያ ሺህ) ሆኖ የተጨማሪ እሴት ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፤ ንብረቱን ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀድም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናት ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጡበት ሰዓት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመሄድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አሳንሶም ሆነ አስበልጦ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ሳያደርግ ቢቀር ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ የሚሆን ሲሆን ንብረቱ በድጋሚ በሐራጅ ተሸጦ ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ዝቅው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፀፀም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
A domestic weaving machine (with spinning and warping parts) is being sold at auction by the Federal Courts Execution Office. Bidders must deposit a CPO equal to one-quarter of the starting estimate; amounts above or below disqualify. The winner must deposit the full amount within 15 days.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender