የደንበኞች ውል ማዋዋያ ኮንትራት ፋይል ሕትመት ግዥ (ኢ/ኤ/አ/ሸገ/ሪ/ግ/ጨ/003/2019) - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/ሸገ/ሪ/ግ/ጨ/003/2019
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን በስር ለሚገኙ ደንበኞች አገልግሎት ማስከፈያ የደንበኞች ውል ማዋዋያ ኮንትራት ፋይል ሕትመት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
| የዕቃው አይነት | የመዝጊያ ቀን እና ሰዓት | የመክፈቻ ቀን እና ሰዓት | የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ |
| የደንበኞች ውል ማዋዋያ ኮንትራት ፋይል | ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት | ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት | ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) |
ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨ.እ.ታ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና ከገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚል ማስረጃ ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ https://epgs.ppa.gov.et ድህረ ገጽ ላይ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፤
- በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000482105592 EEU-ፊንፊኔ ዙሪያ ዲስትሪክት በሚለው በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- አድራሻ፡- 22 ዶንቦሮ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን ስቶሮች ቼይን ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ከላይ በሠንጠረዡ ውስጥ በተገለፀው መሠረት ሆኖ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ሲ.ፒ.ኦ / CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) "Ethiopian Electric Utility-Sheger Region" ስም የተዘጋጀ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከባንክ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በአንድ ላይ በማድረግ «ኦሪጅናል እና ኮፒ» በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/ሸገ/ሪ/ግ/ጨ/003/2019 የሚል በማድረግ እስከ ጥቅምት 16/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተራ ቁጥር 5 ላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን በዚያው ቀን ጥቅምት 16/2019 ዓ.ም 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ጨረታው ከላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251-011-522-65-04 መደወል ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Electric Utility Sheger Region seeks sealed bids from eligible firms to print customer contract agreement files for customer service billing. Bidders must hold a renewed trade license, VAT certificate, TIN, and tax clearance, and be registered on the government supplier portal.
