Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency (የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ)
  • Address ልደታ ክፍለ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ/የኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ጫፌ አናኒ ህንጻ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-8340-636
  • Website
  • Deadline30 Oct 2026, 11:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400(አራት መቶ ብር)
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ጨረታ መናኛ ዋጋ 20% (CPO)
  • opening dateጥቅምት 20/2019 ዓ.ም ከጥዋቱ በ5:00 ተዘግቶ በዕለቱ በ5:15
  • Categories 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles , Generators , Disposal Sale

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ በቢሮ፣ዞን፣ከተማና ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ሞተር ሳይክሎችና ጄኔሬተሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency (የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ)


ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 04/2019

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ በቢሮ፣ዞን፣ከተማና ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ሞተር ሳይክሎችና ጄኔሬተሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም ድረስ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን፤

  1. የኤጀንሲው አድራሻ ፡አዲስ አበባ፣ ልደታ ክፍለ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ/የኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት፣ ጨፌ አናኒ ህንጻ ከሚገኘው የኤጀንሲው የግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3rd Floor) ቢሮ ቁጥር-03 በመቅረብ የማይመለስ ብር 400.00/አራት መቶ ብር ብቻ/በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ከመንግስት ንብረት ዋጋ ግምትና ሽያጭ ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3rd Floor) ቢሮ ቁጥር -02 መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2:30–6:30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7:30 1:00 ሰዓት ብቻ ነው፡፡
  3. የንብረቶቹን ሁኔታ እስከ ጥቅምቲ 19/2019 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2:30–6:30 እና ከሰዓት ከ7:30-1:00 ሰዓትድረስ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለፀው ቦታ በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም ከቢቱ 5:00 ድረስ በኤጀንሲው ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም ከጥዋቱ በ5:00 ተዘግቶ በዕለቱ በ5:15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ መናኛ ዋጋ 20% /ሃያ ከመቶ /የጨረታ ማስከበሪያ CPO የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ. በማዘጋጀትና ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቬሎፕ ውስጥ በመከተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

CPO ለማሰራት

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ

Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-1-83 40-636

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ

✨ messages.ai_summary
The Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency invites bidders to an open tender for the sale of used vehicles, motorcycles, and generators owned by various Oromia offices, located across bureaus, zones, cities, and districts. Bidders must submit prices in sealed envelopes with a 20% CPO bid security.
Save Tender